ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ንግግር ለማድረግ የምክርቤቱን ጥሪ መቀበላቸውን መግለጫው አስታውቋል
46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፕሬዚዳንታዊ ሥራቸውን የጀመሩበትን መቶኛ ቀን ምክንያት በማድረግ ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ የመጀመሪያ ንግግራቸውን ያደርጋሉ፡፡
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ “የዚህን ታሪካዊ ወቅት ችግሮች እና ዕድሎች ለመፍታት ራዕይዎን ያካፍሉን” በማለት አፕሪል 14 በፃፉት በደብዳቤ ፕሬዝዳንቱን መጠየቃቸው ይታወሳል ፡፡
ጥሪውን ባይደን መቀበላቸው ዋይት ሀውስ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
በዚህ መሰረትም ፕሬዝዳንት ባይደን በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ንግግር ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ባይደን በሚያደርጉት ንግግር ታድያ በኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት ከምክር ቤት አባላት ውጭ እንግዶች እንደማይታደሙበት ኤኤፍፒ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ከፕሬዚዳንቱ ንግግር በኋላ የደቡብ ካሮላይና ሴናተር ቲም ስካት የሪፐብሊካኑን ምላሽ ንግግር የሚያሰሙ ይሆናል።ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት በኮቪድ-19 ምክንያት ጭምብል ያደርጋሉ ተብሏል፡፡