አሜሪካ ጭፍጨፋውን “ዘርማጥፋት” ያለችው ለተጠቂዎቹ ክብር ለመስጠት እንጂ እገሌ ነው አጥፊው ለማለት አይደለም ብላለች
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በኦቶማን ኢምፓየር የመጨረሻ አመታት በፈረንጆቹ 1955 የተካሄደውን ጭፍጨፋ “ዘርማጥፋት” ነው ብሎ እውቅና መስጠት ሰለባዎችን ለማክበር እብጂ አጥፊው እገሌ ነው ለማለት አይደለም ብለዋል፡፡
የ“ዘርማጥፋት” ማጥፋት ወንጀሉን ፈጽማዋለች የምትባለው ቱርክን አሜሪካ አሁንም ወሳኝ የኔቶ አጋር አድርጋ እንደምትመለከታት የጆ ባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ ባለስልጣን ለሮተርስ እንደገለጸው አርብ እለት ጆ ባይደን ከቱርኩ ፕሬዘዳንት ሪሲፕ ታይፕ ኤርዶሃን ጋር ያደረጉት የስልክ ንግግር ቀጥተኛ ነበር ብሏል፡፡
በስልክ ቆይታቸው ባይደን ስለዘርማጥፋቱ አዲስ ነገር ለማስታወቅ እንዳቀዱ ለኤርዶሃን ነግረዋቸዋል፤ ባለፉት ሁለት አመታት እየተቀዛቀዘ ስለመጣው የቱርክና የአሜሪካ ግንኙነት በደንብ መወያየታቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡
ዶ ባይደን ከፕሬዘዳንት ኤርዶሃን ጋር በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ፋላጎት ገልጸዋል፤ በሰኔ ወር በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ለመገናኘት እድል እንደሚኖራቸውም ተናግረዋል፡፡