ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬ ውሏቸው የዱባይ 2020 ኤክስፖን ጉብኝተዋል
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ፕሬዝዳንት ኬንያታ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ያቀኑ ሲሆን፤ ከአቡዳቢ አልጋወራሽ እና ከዩኤኢ ምክትል ጦር አዛዥ ከሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በአካባቢያው፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያም በአቡዳቢ ተወያይተዋል፡፡
መሪዎቹ በተለይም ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና እና ሌሎች የጋራ አጀንዳዎች ዙሪያ የተወያዩባቸው አጀንዳዎች ናቸው።
ፕሬዝዳንት ኬንያታ በዛሬው ውሏቸው በዱባይ እየተካሄደ ያለውን 2020 ኤክስፖ የጎበኙ ሲሆን፤ በኤክስፖው ላይ የኬንያ ብሄራዊ ቀን በዓል ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።
የአቡዳቢ አልጋወራሽ እና የዩኤኢ ምክትል ጦር አዛዥ ከሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ኬንያ ባሳለፍነው ወር ላይ በሀውሲ ታጣቂዎች የደረሰውን የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ማውገዟን አመስግነዋል፡፡
ዩኤኢ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ጥብቅ ወዳጅነት መመስረቷን የተናገሩት አልጋወራሹ በተለይም በንግድ፣ በሰላምና ደህንነት እንዲሁም በተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ ዘርፎች ከአፍሪካ አገራ ጋር እየሰራች መሆኗንም አክለዋል።
ፕሬዝዳንት ኬንያታ በበኩላቸው ኬንያ ከኮሮና ቫይረስ ጉዳት እንድታገገም ዩኤኢ ላደረገቸው ድጋፍ መስጋና አቅርበው አገራቸው የልማት ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ተንግረዋል።