ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ቱርክ እና አረብ ኢምሬትስ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ የጋራ ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ግንኙነትን ለማዳበር እና ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ የጋራ ፍላጎት ማሳየታቸውን አፅንኦት ተናግረዋል፡፡
የቱርክ ፕሬዝዳንት በዚህ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጉብኝታቸው የተሰማቸውን ደስታ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው "ትዊተር" ይፋዊ አካውንታቸው ገልፀዋል፡ “የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጉብኝታችንን ዛሬ በስኬት አጠናቀናል” ብለዋል፡፡
አክለውም "ያደረግናቸው ስብሰባዎች 13 ስምምነቶችን በመፈራረማችን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማዳበር እና ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ የጋራ እና ጠንካራ ፍላጎት ያሳየ ነበር" ብለዋል።
የቱርክ ፕሬዝዳንት "እነዚህ ስምምነቶች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራሉ፣ ለተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ደህንነት እና መረጋጋት ያላቸውን ድጋፍ አፅንዖት ይሰጣሉ፡፡"
ፕሬዝዳንቱ አክለውም "የባህረ ሰላጤው አካባቢ ደህንነት የቱርክ የፀጥታ አካል ነው" በማለት በቱርክ እና ኤምሬትስ ግንኙነት መሻሻል የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በመጪዎቹ ጊዜያት ወደፊት እንደሚራመዱ ተስፋ አድርገዋል።
"ለጋራ ጥቅማችንና ለአካባቢያችን የወደፊት እጣ ፈንታ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከባበር እና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ጥረታችንን ለማስቀጠል ቆርጠናል" ብለዋል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለሁለት ቀናት ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡
በፕሬዚዳንት አውሮፕላን ማረፊያ ሼክ ማንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፕሬዝዳንት ጉዳዮች ሚኒስትር እና በርካታ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
የአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ይፋዊ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ላደረጉት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንግዳ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን አቀባበል አድርገውላቸው ነበር፡፡