ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጥምቀትን አከበሩ
ፕሬዝዳንቱ በበረዷማው የመጠመቂያ ስፍራ ተጠምቀዋል
ሩሲያ የጥምቀት በዓልን ከሚያከብሩ ሀገራት መካከል አንዷ ነች
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጥምቀትን አከበሩ፡፡
የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች በድምቀት ከሚያከብሯቸው በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል በምስራቅ አውሮፓ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ በመከበር ላይ ነው፡፡
በዓሉን ከሚያከብሩ ሀገራት መካከል አንዷ በሆነችው ሩሲያም እየተከበረ ሲሆን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተጠምቀዋል፡፡
የ71 ዓመቱ ቭላድሚር ፑቲን በረዶ በሰራው የመጠመቂያ ስፍራ ሲጠመቁ የሚያሳይ ምስል የክሪምሊን ቤተ መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የተጠመቁበት ስፍራ ያልተገለጸ ሲሆን በዓሉ በመላው ሩሲያ በመጠመቅ እና ሌሎች እምነቱ በሚያዛቸው ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡
ጥምቀትን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያከብሩት የዓለም ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በ1952 የተወለዱት እና የህግ ምሩቁ ቭላድሚር ፑቲን ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት ለረጅም ዓመታት የስለላ ባለሙያ ሆነው ሰርተዋል፡፡
የውትድርና እና ስለላ ሙያን እንደሚወዱ የሚናገሩት ፑቲን በጀርመን ለረጅም ዓመታት የኬጂቢ ባለሙያ ሆነው የሰሩ ሲሆን ከሩስኪ ቋንቋ በተጨማሪም እንግሊዘኛ እና ጀርመንኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ፡፡
ላለፉት 24 ዓመታትም ሩሲያን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ ያሉት ቭላድሚር ፑቲን ለተጨማሪ ዓመታት ፕሬዝዳንት ለመሆንም ከወራት በኋላ ምርጫ ያካሂዳሉ፡፡