በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ፣ በጎንደር፣ በባቱ፣ በምንጃር ኢራንቡቲና የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍልች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል
በየዓመቱ ጥር 11 ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ዛሬ ተከብሮ ውሏል።
የጥምቀት በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው በድምቀት ተከብሮ ውሏል።
የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ በጽዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሯል።
በዓሉ በጎንደር ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።
በተጨማሪም በዓሉ በባቱ ደንበል ኃይቅ፣ በባህር ዳር፣ በሃዋሳ በኃቆች ላይ ተከሯል።
በጅማ፣ በሻሸመኔ፣ በሆሳዕና፣ በደብረ ብርሃን፣ በነቀምቴ ፣በጋምቤላ ፣ በምንጃር ኢራንቡቲ እና በተለያዩ አካባቢዎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ ውሏል።
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር በዓል ነው።