ጥምቀትን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያከብሩት የዓለም ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበር በዓል ነው
ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬንና ጆርዳን ጥምቀትን በማክበር በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ሀገራት ናቸው
ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ዓመታዊ በዓሎች አንዱ ነው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ያሉ የእምነቱ ተከታዮች የጥምቀት በዓልን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ለዘመናት እያከበሩ እዚህ ደርሰዋል።
በዓሉ ዛሬ ማለትም ጥር 11 የሚከበርባው ሀገራት ውስጥም ኢትዮጵያ ኤርትራ፣ ሩሲያ እና ጆርዳን ተጠቃሽ መሆናቸው ይታወቃል።
ኢትዮጵ በዓሉን በትናናው እለት በከተራ ዛሬ ደግሞ ታቦታቱ ባደሩባቸው ጥምቀተ ባህር በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እና ስርዓት ጥምተው በመከበር ለይ ይገኛል።
የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በተመሳሳይ ኃይማኖታዊ ስርዓት ነው ተከብሮ የሚለውለው።
ከ90 ሚሊየን በላይ የኦርቶድክስ እምነት ተከታዮች ያሏት ሩሲያም የጥምቀት በዓልን በድምቀት ከሚያከብሩ ሀገራ መካከል ተጠቃሽ ነች።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን እና ስላሴዎችን ለማስታወስ በበረዶ ውሃ ውስጥ ራሳቸውን ሶስት ጊዜ ይነከራሉ።
የሩሲያ ኦርቶዶክሳዊያን ለሶስት ጊዜያት ራሳቸውን በበረዶ ውሃ ውስጥ መንከር ሀጢያታቸውን ያነፃል ብለው ያምናሉ።
የእምነቱ ተከታዮች በጥምቀት ወቅት ሁሉም ውሃ የተቀደሰ መሆኑን የሚያምኑ ሲሆን፥ በረዶውም ጤናቸው ላይ በጎ ተፅዕኖ እንዳለውም ያምናሉ።
ዩክሬናውያንም በረዶን በመስቀል ቅርጽ ከቆረጦ በኋላ በክስ ባለ ውሃ ምስጥ ራሳቸውን በመንከር የጥ፣ቀት በዓልን የሚያከብሩ መሆኑ ይታወቃል።
በተወሰኑ የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችም በጥልቁ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ በዋና ውድድር የታጀበን የጥምቀት በዓል ያሳልፋሉ።
በቦስኒያ እና ሄርዞጎቪኒያ የሚገኙት የእምነቱ ተከታዮች በቄሶች ወደ ውሃ የተጣለውን የእንጨት መስቀል ለመያዝ የሚደረግ የዋና ፉክክር ይደረጋል።
በዚህ የዋና ውድድር መስቀሉን መያዝ የቻለው እና ወደ መሬት የመለሰው ግለሰብ ዓመቱን በሙሉ የተባረከ ይሆናል ብለውም ያምናሉ።