የሩሲያዋ የድንበር ከተማ የጥምቀት በዓልን ሰረዘች
ከተማዋ ለዩክሬን ቅርብ ስለሆነች መልቲፕል ሮኬት ላውንቸርን ጨምሮ ቀላል እና ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች በመጠቀም ማጥቃት ይቻላል
የሩሲያዋ የድንበር ከተማ በዩክሬን የጥቃት ዛቻ ምክንያት የኦርቶዶክስ የጥምቀት በዓል እዳይከበር አደረገች
የሩሲያዋ የድንበር ከተማ የጥምቀት በዓልን ሰረዘች።
የሩሲያዋ የድንበር ከተማ በዩክሬን የጥቃት ዛቻ ምክንያት የኦርቶዶክስ የጥምቀት በዓል እዳይከበር አደረገች።
ዩክሬን፣ ጦርነቱ ሁለተኛ አመቱን ሊይዝ እየተቃረበ ባለበት ወቅት አዲስ ስትራቴጂ እየቀመረች በመሆኑ በዩክሬን ድንበር የምትገኘው የሩሲያዋ ከተማ በዛሬው እለት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል እንዲሰረዝ ማድረጓን ኤፒ ዘግቧል።
የቤልጎሮድ ከተማ ምዕመናን ውሃ ውስጥ በመነከር የሚያከብሩትን የጥምቀት በዓል እንዲሰረዝ አድርጋለች።
ከዩክሬን ጋር ድንበርተኛ በሆነችው ትልቋ የሩሲያ ከተማ ቤልጎሮድ 340ሺ ሰዎች የሚኖሩባት ሲሆን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ጥቃቶች በተደጋጋሚ አጋጥመዋታል።
ከተማዋ ለዩክሬን ቅርብ ስለሆነች መልቲፕል ሮኬት ላውንቸርን ጨምሮ ቀላል እና ተንቀሳቃሽ መሳሪያዎች በመጠቀም ማጥቃት ይቻላል።
ባለፈው ታህሳስ 30 በማዕከላዊ ቤልጎሮድ በተፈጸመ ጥቃት 21 ሰዎች መገደላቸውን እና 110 ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት መግለጻቸው ይታወሳል።
ጥቃቱ ሩሲያ ዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈች ወዲህ በሩሲያ ምድር ላይ የተፈጸመ ከባድ ጥቃት ነው ተብሏል።