የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ወታደሮች “ለጦርነት እንዲዘጋጁ” አዘዙ
ባለፈው ወር በተካሄደው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ገዝፎ ስለመታየቱ ተነግሯል
ዢ ጂንፒንግ በቅርቡ ታሪካዊ በተባለ ውሳኔ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን የቻይና ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የቻይና ወታደሮች “ለጦርነት እንዲዘጋጁ” ማዘዛቸው ተሰምቷል።
የቻይና ብሄራዊ ደህንነት አለመረጋጋት መጨመርና ጥርጣሬ ከፍ ማለት እየተስተዋለ መሆኑንም አክለዋል።
ፕሬዚዳንቱ “መላው ጦር አቅሙን ሙሉ ለውጊያ ዝግጁ ማድረግ እና ስራውን በሙሉ ማከናወን ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል።
የፓርቲውን ፣የወታደራዊ እና የርዕሰ ብሄርነት ሦስት ግንባር ስልጣኖችን በመያዝ ከፓርቲው መስራች ማኦ ዜዶንግ በመቀጠል የ10 ዓመት የስልጣን ቆይታቸውን አጠናቅቀው በስልጣን ላይ የቆዩ ብቸኛ መሪ ናቸው።
ፕሬዝዳንት ዢ ወታደሮች የብሄራዊ ኮንግረስ መርሆችን በጥልቀት እንዲያጠኑ፣ ለህዝብም እንዲያሳውቁ እና እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
የሀገር መከላከያን እና ወታደራዊ ኃይሉን የበለጠ ለማዘመን ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱም መመሪያ ሰጥተዋል ሲሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኸን ዥንዋን ጠቅሰው ዘግበዋል።
ባለፈው ወር በተካሄደው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት በላቀ ብሄራዊ ደህንነት ገዝፎ ስለመታየቱ ተነግሯል።
በተለይም የታይዋን ጉዳይ ቀጣዩ የዓለም ጦርነት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋትን ደቅኗል።
ቻይና የግዛቴ አካል የምትላት ታይዋን ከምዕራባዊያኑ ጋር እየመሰረተችው ያለው ወዳጅነት ለደህንነት በተጠንቀቅ መቆም ቁልፍ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።