ይህን የአለም ዋንጫ አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በትብብር አዘጋጅተውታል
በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ስፔን እና እንግሊዝ በነገው እለት ይጋጠማሉ።
ይህን የአለም ዋንጫ አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በትብብር አዘጋጅተውታል። ሩብ ግማሽ መግባት የቻለችው ተባባሪ አዘጋጇ አውስትራሊያ በስዊድን 2 ለ0 ተሸንፋለች።
ያለፉትን የዓለም ዋንጫ ውድድር ያሸነፉ ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው፦
የሴቶች የዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ከፈረንጆቹ 1991 ዋንጫ ያነሱ ብሔራዊ ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው።
ዓ.ም አሸናፊ ተጋጣሚ ውጤት
1991 አሜሪካ ኖርዌይ 2-1
1995 ኖርዌይ ጀርመን 2-0
1999 አሜሪካ ቻይና 0-0*(5-4p)
2003 ጀርመን ስዊድን 2-1
2007 ጀርመን ብራዚል 2-0
2011 ጃፖን አሜሪካ 2-2(3-1p)
2015 አሜሪካ ጃፖን 5-2
2019 አሜሪካ ኔዘርላንድስ 2-0
የዘንድሮ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ፣ ብራዚል እና ጀርመንን የመሳሰሉ ትላልቅ ብሔራዊ ቡድኖች በጊዜ በመሰናበታቸው ያልተጠበቀ ክስተት አስተናግዷል። በሌላ በኩል ብዙ ግምት ያልተሰጣቸው የሞሮኮ አይነት ቡድኖች ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ታይተዋል።