ኋይት ሀውስ በቻይና ውስጥ የአሜሪካ ኢንቨስትመንቶች የሚገድብ እቅድ መንደፉ ተነገረ
ፕሬዝዳንት ባይደን ሚስጥራዊነት ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ለማጣራት ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል
እቅዱ የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል
ዋይት ሀውስ በቻይና ውስጥ አንዳንድ የአሜሪካ ኢንቨስትመንቶች የሚያሰጉ ቴክኖሎጂዎችን ለመገደብ ያለውን እቅድ በዝርዝር ያቀርባል ተብሏል።
ባለሀብቶች ሌሎች ኢንቨስትመንቶችንም ለመንግስት ማሳወቅ እንዳለባቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል።
እቅዶቹ የቻይናን ዘመናዊ ወታደራዊ አቋም የሚደግፉ እና የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማዳበር የአሜሪካን ካፒታል እና እውቀት ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል ያለመ ነው።
ሮይተርስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሚስጥራዊነት ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ለማጣራት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ትእዛዝ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት በቻይና ውስጥ በአሜሪካ ኢንቨስትመንት ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ገደቦች ውስን ኢላማ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።
የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሰለቫን "እነዚህ የተወሰኑ እርምጃዎች ናቸው" ብለዋል።
አማካሪው ቤጂንግ እንደምትለው ‘የቴክኖሎጂ እገዳ’ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
የሀገሪቱ የንግድ ሚንስትር ጂና ሬይሞንዶ አስተዳደሩ ገደቡ ከመጠን በላይ ሰፊ እንደማይሆን ገልጸዋል።
ሰፊ እርምጃ ከሆነ የአሜሪካን ሰራተኞች እና ኢኮኖሚውን ይጎዳል ብለዋል። ዋይት ሀውስ በቻይና ውስጥ አንዳንድ የአሜሪካ ኢንቨስትመንቶች የሚያሰጉ ቴክኖሎጂዎችን ለመገደብ ያለውን እቅድ በዝርዝር ያቀርባል ተብሏል።
ባለሀብቶች ሌሎች ኢንቨስትመንቶችንም ለመንግስት ማሳወቅ እንዳለባቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግረዋል።
እቅዶቹ የቻይናን ዘመናዊ ወታደራዊ አቋም የሚደግፉ እና የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማዳበር የአሜሪካን ካፒታል እና እውቀት ጥቅም ላይ እንዳይውል ለመከላከል ያለመ ነው።
ሮይተርስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሚስጥራዊነት ያላቸው ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ለማጣራት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ትእዛዝ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት በቻይና ውስጥ በአሜሪካ ኢንቨስትመንት ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ገደቦች ውስን ኢላማ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።
የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሰለቫን "እነዚህ የተወሰኑ እርምጃዎች ናቸው" ብለዋል።
አማካሪው ቤጂንግ እንደምትለው ‘የቴክኖሎጂ እገዳ’ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
የሀገሪቱ የንግድ ሚንስትር ጂና ሬይሞንዶ አስተዳደሩ ገደቡ ከመጠን በላይ ሰፊ እንደማይሆን ገልጸዋል።
ሰፊ እርምጃ ከሆነ የአሜሪካን ሰራተኞች እና ኢኮኖሚውን ይጎዳል ብለዋል።