ለዩክሬን የሚደረግ ወታደራዊ ድጋፍን የተቃወሙ ጀርመናውያን አደባባይ ወጡ
በርሊን ሊዮፓርድስ 2 የተሰኘውን ታንክ ለኬቭ ለማቅረብ መስማማቷ አንድ አመት የደፈነውን ጦርነት ይበልጥ ያራዝመዋል ብለዋል
ስልፈኞቹ “የኛ ጦርነት አይደለም” የሚልና ሌሎች መልዕክቶችም በሰልፉ ላይ ተንጸባርቀዋል
ጀርመን በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ያላት ተሳትፎ በሀገር ቤት ተቃውሞ አስነስቷል።
ከ10 ሺህ በላይ ጀርመናውያን በበርሊን አደባባይ ወጥተው በይፋ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ነው ሮይተርስ የዘገበው።
- ከጦርነቱ ከአንድ ዓመት በኋላ ቻይና የዩክሬንን ቀውስ ለመፍታት ያላትን ተነሳሽነት በዝርዝር አሳወቀች
- ሩሲያ የፕሬዝዳንት ባይደንን የዩክሬን ጉብኝት “ቴአትር” ነው ስትል አጣጣለች
ከጦርነቱ ከአንድ ዓመት በኋላ ቻይና የዩክሬንን ቀውስ ለመፍታት ያላትን ተነሳሽነት በዝርዝር አሳወቀች
የጀርመን ግራ ዘመም ፓርቲ ዳይ ሊንኬ ያሰተባበረው የተቃውሞ ስልፍ ላይ ጀርመን በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ለአንዱ ከመወገን ይልቅ ገለልተኛ እንድትሆን ተጠይቋል።
በየቀኑ “ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሞቱበት ጦርነት” ላይ ተሳትፎ ማድረግ ደም መፋሰሱን ያስቀጥለዋል እንጂ መፍትሄ አይሆንም፤ በርሊን የማደራደር ሚና ነው ሊኖራት የሚገባው የሚሉና ተያያዥ ሃሳቦችም እየተነሱ ነው ተብሏል።
የተቃውሞ ስልፉን ያዘጋጀው ፓርቲ በድረ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ጀርመን ለዩክሬን የምታደረገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ሶስተኛው የአለም ጦርነትን ሊያስነሳ ይችላል።
ጀርመን “ሊዮፓርድስ 2” የተሰኘውን ታንክ ለኬቭ ለመስጠት ቃል መግባቷ ይታወሳል።
ከአሜሪካ በመቀጠል ለኬቭ በርካታ የጦር መሳሪያ በማቅረብ ላይ ያለቸውም በርሊን ናት።
በርሊን ታንኮቹንም ሆነ ሌሎች መሳሪያዎችን ወደ ኬቭ እንድትልክ ከምዕራባውያን ከፍተኛ ጫና እንደተደረገባት አይዘነጋም።
ጀርመናውያኑ በዛሬው ሰልፍ ላይ “ጦርነቱ የኛ አይደለም፤ በድርድር እንዲፈታ ጥረት ማድረግ ይሻላል” ሲሉ ተደምጠዋል።
የጀርመን ፖሊስ 1 ሺህ 400 የጸጥታ ሰራተኞችን ማሰማራቱን ያሳወቀ ሲሆን፥ የተቃውሞ ሰልፉ በቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች የመጠለፍ ምልክት አላሳየም ብሏል።
የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር ክርስቲያን ሊንድነር የተቃውሞ ስልፉ በሰላማዊ ሁኔታ መካሄዱን ቢገልጹም፥ “አሁን ከዩክሬን ጎን ያልተሰለፈ በታሪክ በመጥፎ ገጽ ላይ ይቀመጣል” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይይ አስፍረዋል።