ለዩክሬን ጦርነት “ምዕራባውያንን ተጠያቂ ያደረገው” የፕሬዝዳንት ፑቲን የፓርላማ ንግግር
ምዕራባውያን ዩክሬንን ለማስታጠቅ 150 ቢሊየን ዶላር ማውጣታቸውንም ፑቲን ገልጸዋል
ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ “ሩሲያ ወደ ዩክሬን ጦርነት የገባችው ራሷን ለመከላከል ነው” ብለዋል
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂዎቹ ምእራባውያን ናቸው ሲሉ ከሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አንድ ዓመት ሊሞላው ቀናት ብቻ በቀሩት የዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ አንደኛ ዓመት ዋዜማ ላይ በሀገሪቱ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር "በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እየኖርን ነው" ብለዋል።
- የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጆ ባይደን ጋር መነጋገሩ “አስፈላጊነቱ ብዙም አይታየኝም ” አሉ
- የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጆ ባይደን ጋር መነጋገሩ “አስፈላጊነቱ ብዙም አይታየኝም ” አሉ
ፑቲን ከጦርነቱ በፊት የነበረው ሁኔታ መለስ ብለው ሲያስታውሱም “በወቅቱ የነበረው የምእራባውያን ተማጽኖ እና ቃል ዩክሬንን ለጦርነት ለማዘጋጀት ጊዜ ለመግዛት የሚደረግ ሽፋን ብቻ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።
ወታደራዊ ዘመቻው ከመጀመሩ በፊትም ቢሆን በኪቭ እና በምዕራባውያን መካከል ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑ የሚያመለክቱ የጦር መሳሪያ አቅርቦትን የተመለከቱ ንግግሮች እንደነበሩም ገልጸዋል።
ፑቲን የፓርላማ ንግግራቸውን ሲቀጥሉም “ምእራባውያንየዩክሬን ጦርነት ዓለም አቀፋዊ የማድረግ ፍላጎት ነበራቸው” ብለዋል።
ሞስኮ ከጅምሩ አንስቶ ከምእራቡ ዓለም ጋር ለመነጋገር በሯን ክፍት አድርጋ ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይሁን እንጂ ምእራባውያን ግጭቱን ከማርገብ በተቃራኒ ይበልጥ እንዲጋጋል አድርገውታል ሲሉ ከሰዋል። ምዕራባውያን ዩክሬንን ለማስታጠቅ 150 ቢሊየን ዶላር ማውጣታቸውን በመጠቆም፡፡
ለጦርነቱ ኃላፊነቱን የሚወስዱት ምእራባውያን መሆናቸውን የገለጹት ፑቲን፤ ሩሲያ ወደ ዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ የገባችው ራሷን ለመከላከል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
“እነሱ ጦርነቱን ጀመሩት እኛም ለመከላከል ሁሉም ነገር አደርግን” ብለዋል ፑቲን፡፡
ፑቲን አክለውም ሩሲያን ለማሽመድመድ በማሰብ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ ያዘነቡት የኢኮኖሚ ማእቀብ “አልተሳካም” ሲሉ ተደምጠዋል።
የተለያዩ ሀገራት በሩሲያ ላይ ተመልሶ እራሳቸውን በዋጋ ግሽበትና በኢነርጂ ቀውስ እየቀጣቸው መሆኑም በአብነት አንስተዋል ፑቲን።
አሜሪካ በዓለም ላይ ብዙ የጦር ሰፈር ያላት እና ስምምነቶችን በተናጠል የምትጠስ ሀገር ናት ሲሉም ከሰዋል፡፡
በተመሳሳይ “በዓለም ዙሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኔቶ ወታደራዊ ካምፖች አሉ፤ ይህንን ለማየት ካርታውን መመልከት በቂ ነው” በማለትም ከየአሜሪካ አጋሮች ስብስብ የሆነውን ኔቶን ወቅሰዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡