ኮሮና እንደሚከሰት የተነበየው ሰው በ2025 ይፈጠራል ያለው አስደንጋጭ ነገር ምንድን ነው?
በአመቱ የሀይማኖትና የብሔር ግጭቶችም እንደሚበረክቱ ግለሰቡ ተንብዮዋል
የ38 አመቱ የለንደን ከተማ ነዋሪ በ2025 3ተኛው የአለም ጦርነትን ጨምሮ ሌሎች አስከፊ ሁነቶች ይከሰታሉ ብሏል
የኮቪድ ወረርሽኘን ከዓመታት በፊት የተነበየው ራሱን ተንባይ (ሳይኪክ) ብሎ የሚጠራው ግለሰብ በ2025 አለም ከባባድ ቀውሶችን እንደምታስተናግድ ተንብዮዋል፡፡
ነዋሪነቱን በለንደን ያደረገው ኒኮላስ አውጁላ የተባለው የ38 ዓመቱ “የሂፕኖቴራፒ” ባለሙያ አመቱ በአለም ላይ ርህራሄ የጎደለበት ይሆናል ብሏል።
“የሶስተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ስጋትን ጨምሮ በሃይማኖት እና በብሔርተኝነት ስም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶችን እና ጥቃቶችን እንመለከታለን” ሲል ተንብዮአል።
2024 ከመግባቱ በፊት የትራምፕን አሸነፊነት ቀድሞ መተንበይ የቻለው ግለሰብ ራዕዮቹን መቆጣጠር እንደማይችል እና ተመልክቸዋለሁ ባለው ራዕይ መሰረት በ2025 አመት አጋማሽ የሶስተኛ የአለም ጦርነት ሊከሰት ይችላል ነው ያለው፡፡
ደይሊ ሜይል ባወጣው ዘገባ የቅሪተ አካል ነዳጆች አጠቃቃም ማደግ የባህር ከፍታ መጨመር፣ ከባድ ዝናብ እና ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የተፈጥሮ አደጋ በብዛት ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቁን አስነብቧል፡፡
በተጨማሪም ሰደድ እሳትን ጨምሮ በቅርቡ በአሜሪካ በሰሜን ካሮላይና የተከሰተው አውሎ ንፋስ ፣ የደን ቃጠሎ እና ሌሎችም የተፈጥሮ አደጋዎች በአመቱ ለሰው ልጆች እና ለእንስሳት ህይወትን ከባድ እንደሚያደርግ ጠቅሷል፡፡
ወጣቱ ከ17 አመቱ ጀምሮ ስለ ወደፊቱ የመጀመሪያ ራዕይ ከተመለከተ በኋላ ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ትምህርትን አቁሞ ወደፊቱን ሲተነብይ እንደቆየ ተነግሮለታል፡፡
ትንበያ እና ራዕዮቹ ያለፈውን ጊዜ ፣ ዛሬ እና ነገን መነሻ በማድረግ የሚከሰቱ መሆናቸውን የሚናገረው ወጣቱ የትንበያ አቅሙን ለማሳግ በቻይና እና በሂማሊያ ተራሮች በሚገኙ የተለያዩ መንፈሳዊ ተቋማት ላይ ትምህርት መማሩን ይገልጻል፡፡
ራዕዮቹም በድምጽ በምልክት እንዲሁም በጭንቅላቱ ውስጥ በሚፈጠር ሀይለኛ ድምጽ ወደ እርሱ እንደሚመጡ ነው የሚናገረው፡፡