ለወራት ህዝባዊ እይታ ርቀው የቆዩት ኢታማዦር ሹም ገራሲሞቭ ከፑቲንን ጋር ታይተዋል
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ የዩክሬን አቅንተው ከጦር ጀነራሎቻቸውና ከፍተኛ መኮንኖች ጋር መምከራቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
ምክክሩ ዩክሬን በመልሶ ማጥቃት ዘመቻዋ በደቡብ ምስራቅ ግንባር ድል እየተቀዳጀሁ ነው ማለቷን ተከትሎ የመጣ ነው።
በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን ጦርነት የከፈተችው ሩሲያ፤ እርምጃውን "ልዩ ወታደራዊ ተልዕኮ" በሚል ትጠራዋለች።
ክሬምሊን የሩሲያው ጦር ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ፑቲን በዩክሬን ውስጥ የሞስኮን እንቅስቃሴ ከሚቆጣጠሩት ኢታማዦር ሹም ቫለሪ ገራሲሞቭ እና ሌሎች ከፍተኛ የጦር አዛዦች እና መኮንኖች ሪፖርቶችን አዳምጣል።
ሆኖም ክሬምሊን ተደረገ ስለተባለው ውይይት ተጨማሪ መረጃ አልሰጠም።
ሮይተርስ ውይይቱ መቼ እንደተካሄደም አልታወቀም ሲል ዘግቧል።
ይፋ በሆነ ተንቀሳቃሽ ምስል ኢታማዦር ሹም ገራሲሞቭ በምሽት ፑቲንን ሲቀበሉ ታይተዋል።
ከህዝባዊ እይታ ርቀው የነበረው ኢታማዦር ሹም በተለይም ከዋግነር ቅጥረኛ ጦር መሪ ከባድ ትችት ሲሰነዘርባቸው ከርመዋል።
የዩክሬን መልሶ ጥቃት ስር የሰደዱ የሩስያ መከላከያን ለማቋረጥ እየታገለ ሲሆን፤ በሞስኮ ወታደራዊ ኃይል ውስጥም አለመግባባት እንዳለ ተነግሯል።
ሁለቱም ወገኖች ጥቃቅን መንደሮችን በመቆጣጠር ድል አገኘን እያሉ ነው።