ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል የተወሰኑ ግዛቶቿን ለሩሲያ ለመስጠት ልትስማማ እንደምትችል የኔቶ ባለስልጣን ተናገሩ
ዩክሬን በበኩሏ የኔቶን ውሳኔ ፈጽሞ እንደማትቀበለው አስታውቃለች
ኔቶ ለዩክሬን ካሳ በሚል ቃልኪዳኑን እንድትቀላቀል እፈቅዳለሁ ብሏል
ዩክሬን የተወሰኑ ግዛቶቿን ለሩሲያ እንድትሰጥ ኔቶ አሳሰበ።
ለአንድ ሳምንት ልዩ ዘመቻ በሚል የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት 18ኛ ወሩ ላይ ይገኛል።
አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬን ከሩሲያ እየደረሰባት ያለውን ጥቃት እንድትመክት የጦር መሳሪያ ማስታጠቃቸውን ቀጥለዋል።
ጦርነቱን በድርድር ለማጠናቀቅ የተጀመረው የሰላም ጥረት እስካሁን ፍሬ አለማፍራቱ ሲገለጽ ከ30 በላይ ሀገራት ይሳተፉበታል ተባለው የሪያዱ ድርድር አስቀድሞ በሞስኮ ውድቅ ተደርጓል።
የጦርነቱ አድማስ እና ስጋት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ኔቶ ተገዶ ጦርነቱን እንዳይቀላቀል ተሰግቷል።
የኔቶ ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ስቲያን ጀንሰን ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የገባችበትን ጦርነት ለመቋጨት ዩክሬን የተወሰኑ ግዛቶቿን ለሞስኮ እንድትሰጥ ጠይቀዋል።
ዩክሬን በምትኩ የኔቶ አባል አድርጎ መቀበልን እንደ አማራጭነት ያስቀመጡት ሀላፊው ከፍተኛ ትችቶችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።
ዩክሬን በበኩሏ ኔቶ ያቀረበውን ምክረ ሀሳብ ፍጹም ተቀባይነት እንደሌለው ገልጻ በሁኔታው ማዘኗን አስታውቃለች።
ከዩክሬን እና ከተለያዩ አካላት ትችቶችን ያስተናገደው ኔቶ የጽህፈት ቤት ሀላፊውን አስተያየት ወደ ጎን በመተው ኔቶ በዩክሬን ጉዳይ ድጋፉን እንደሚቀጥል ገልጿል።
የቡድን 20 ሀገራት ከአንድ ወር በኋላ በህንድ ኒው ዴልሂ የሚካሄድ ሲሆን ዩክሬን በጉባኤው ላይ እንድትካፈል እስካሁን አልተጋበዘችም ተብሏል።
ሩሲያ የቡድን 20 አባል ሀገር በመሆኗ በጉባኤው ላይ እንደምትገኝ ይጠበቃል ሲል ስካይኒውስ ዘግቧል።