ፖለቲካ
የሩሲያ እና ቻይና ባህር ኃይሎች በፖሲፊክ የጋራ ቅኝት አካሄዱ
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በአንድ ወቅት ከቻይና ጋር "ገደብ የሌለው ወጃድነት" መመስረታቸውን መናገራቸው ይታወሳል
የባህር ኃይሎቹ በልምምዱ ከ6400 በላይ ናውቲካል ማይል እርቀት መሸፈናቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል
የሩሲያ እና የቻይና የባህር ኃይሎች በፖሲፊክ በጋራ ቅኝት ማካሄዳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የሩሲያ እና የቻይና የባህር ኃይል መርከቦች በፖሲፊክ ውቅያኖስ ላይ በጋራ መቃኘታቸውን እና በምስራቅ የቻይና ባህር ልምምድ ማድረጋቸውን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ገጹ እንዳለው የሩሲያ የባህር ኃይል ቡድን እና የቻይና ላይብሬሽን አርሚ(ፒኤልኦ) በአሁኑ ወቅት በምስራቅ ቻይና ባህር ላይ ልምምድ እያደረጉ ነው።
የሁለቱ ሀገራት ባህር ኃይሎች በልምምዱ ከ6400 በላይ ናውቲካል ማይል እርቀት መሸፈናቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ቻይና እና ሩሲያ በእስያ አህጉር ኃያላን ሲሆኑ ሌሎች ሀገራትን ከጎናቸው በማሰለፍ በምዕራባውያን የሚመራውን የዓለም ስርአት ለመቀየር ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
ሁለቱን ሀገራት ያቀፈው ብሪክስ የተሰኘው ጥምረት የዶላርን አለምአቀፍ ተጽዕኖ ለመቀነስ አርምጃዎችን እየወሰደ ነው።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን በአንድ ወቅት ከቻይና ጋር "ገደብ የሌለው ወጃድነት" መመስረታቸውን መናገራቸው ይታወሳል።