ፑቲን በቅርቡ የአሜሪካ ፓትሪዮት አየር መከላከያ ስርአትን የማወደም በቂ አቅም አለን ማለታቸው አይዘነጋም
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የመምታት መብትን በተመለከተ አዲስ ህግ አውጥተዋል።
ህጉ የደህንነት ክፍሎች የድሮን የርቀት መቆጣጠሪያ ምልክቶችን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲቀይሩ፣ የቁጥጥር ፓነሎቻቸውን እንዲነኩ ወይም ድሮኖች እንዲጎዱና እንዲያጠፉ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ ለዩክሬን የምታቀርበውን ፓትሪዮት አየር መከላከያ ስርአትን የሚያወድም በቂ አቅም እንዳላቸው በእርግጠኝነት ሲናገሩ መደመጣቸው አይዘነጋም፡፡
"100 በመቶ እናጠፋዋለን"ም ነበር ያሉት ፑቲን ባለፈው እሁድ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን በተላለፈው ቃለ ምልልስ ከአንድ ጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጡት ምለሽ ።
እሱ (መሳሪያው) “በጣም ያረጀ ነው” እንደ ሩሲያ ኤስ-300 የመከላከያ ስርዓት አይሰራም ያሉት ፑቲን፤ ሩሲያን የፓትሪዮት አየር መከላከያ ስርዓትን ለማክሸፍ "የምንጊዜም መድኃኒት ታገኛለች" ሲሉም ዝተዋል፡፡
ምእራባውያን የተከፋፈለች ሩሲያን ለማየት እየሰሩ ነው የሚል ክስ ሚያቀርቡት ፑቲን፤ የሞስኮ “ዓላማ” ፍጹም የተለየ መሆኑንና እሱም” ሩሲያውያንን አንድ ማድረግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳነቱ ይህን ይበሉ እንጅ አሜሪካም ሆነ ምዕራባውያን ክሬምሊን ላይ የሚያደርጉት ጫና አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
አሜሪካ፤ ፑቲን ያለውን እውነታ በሚገባ ተረድተው ጦራቸውን ከዩክሬን ምድር እንዲያስወጡ ጠይቃለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ " አሜሪካም እና የተቀረው ዓለም ሩሲያ የካቲት 24 በዩክሬን የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተንኳሽ ጦርነት መሆኑን ተገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም ከ 300 በኋላ ቀናት ፑቲን ጦርነቱን ምን (ለማንም የማይበጅ) እንደሆነ ገልጸዋል” ብሏል፡፡
ፑቲንን ጨምሮ በዩክሬን ያለው ግጭት ለረጅም ጊዜያት ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ በማለት ይጠሩት የነበረ ቢሆንም ፑቲን በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ”ጦርነት” ብለው መጥራታቸው የሚታወስ ነው፡፡