ፖለቲካ
የሩሲያ አጋር የሆነችው ቤላሩስ የዩክሬንን ኤስ-300 ሚሳይል መትቼ ጣልኩ አለች
ቤላሩስ የተኮሰው ሚሳይል ሆን ተብሎ ወይም በስህተት መሆን እያጣራሁ ነው ብላለች
መከላከያ ሚኒስቴሩ የተመታው ሚሳይል በቤላረስ ድንበር ውስጥ አርፏል ብሏል
የቤላሩስ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በትናንትናው እለት ቤላሩስ ከዩክሬን በሚያዋስናት ድንበር አቅራቢያ ኤስ-300 የተባለ የዩክሬን ሚሳይን መትቶ ጥሏል፡፡
መከላከያ ሚኒስቴሩ የተመታው ሚሳይል በቤላሩስ ድንበር ውስጥ አርፏል ብሏል፡፡ ቤላሩስ ይህን ያላችው፣ ሩሲያ ከባድ የሚባል የሚሳይል ጥቃት በዩክሬን ከተሞች ላይ እያዘነበች ባለችበት ወቅት ነው፡፡
ቤላሩስ የተኮሰው ሚሳይል ሆን ተብሎ ወይም በስህተት መሆን እያጣራሁ ነው ብላለች፡፡
የሩሲያ ጎረቤት የሆነችው ቤላሩስ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወታደራዊ ዘመቻ ድጋፍ የሰጠች ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡
ሩሲያ እና ቤላሩስ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊትም የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ነበር፡፡ ሩሲያም አጋሯ ለሆነችው ቤላሩስ ዘመናዊ የሆኑ የአየር መከላከያ ሚሳይሎችን አስታጥቃለች፤ይህም በዩክሬን አጋር በሆኑ ምእራባውያን ሀገራት ተቃውሞ ገጥሮባታል፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የተጀመረው፣ ሩሲያ የምእራባውን ወታደራዊ ክንፍ የሆነው ኔቶ ወደ ዩክሬን እና ወደ ቀድሞ ሶቬት ሀገራት እየተስፋፋ ነው በሚል ነበር፡፡ ሩሲያ የኔቶ መስፋፋት የደህንነት ስጋት እንደሚገጥርባት ስትገልጽ ቆይታ ነበር፡፡