ፑቲን ከዩክሬን ጋር የሚደረግ ንግግርን እንደማይቃወሙ ገለጹ
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ሩሲያ በርካታ ግዛቶችን ሳትለቅ ተኩስ ማቆም የማይታሰብ ነው ብለዋል
ፑቲን በአፍሪካ የቀረበው የሰላም እቅድ ለሰላም መሰረት ሊሆን ይችላል፤ነገርግን ዩክሬን የምታደርገው ጥቃት እንዳይሳካ አድርጎታል ብለዋል
ፑቲን ከዩክሬን ጋር የሚደረግ ንግግርን እንደማይቃወሙ ገለጹ
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ከዩክሬን ጋር የሚደረገን የሰላም ንግግር እንደማይቃወሙ ተናግረዋል።
ፑቲን በአፍሪካ የቀረበው የሰላም እቅድ ለሰላም መሰረት ሊሆን ይችላል፤ነገርግን ዩክሬን የምታደርገው ጥቃት እንዳይሳካ አድርጎታል ብለዋል።
ባለፈው አርብ እለት በሴትንፒተርስበርግ የአፍሪካ መሪዎች ያቀረቡትን የሰላም እቅድ እንዲቀበሏቸው ከጠየቁ በኋላ ፑቲን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
"እየተተገበሩ ያሉ የሰላም እቅዱ አንቀጾች አሉ። ነገርግን የተወሰኑ አስቸጋሪ ወይም ለመተግበር የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ።" ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።
ሮይተርስ ባለፈው ሰኔ እንደዘገው የአፍሪካ የሽምግልና ሂደት በተኩስ ማቆም እና እሱን ተከትሎ በሩሲያ እና በምዕራባውያን መካከል በሚደረግ ድርድር እንጀሚጀምር ገልጾ ነበር።
ፑቲን በሰላም እቅድ ውስጥ አንደኛው ነጥብ ተኩስ አቁም ማድረግ ነው ብለዋል። "ነገርግን የዩክሬን ጦር እያጠቃ ነው፣ ጠነሰፊ የሆነ የጥቃት ዘመቻ እያካሄደ ነው... እየተጠቃን ተኩስ ማቆም አንችልም ብለዋል።"
ፑቲን የሰላም ድርድር መጀመርን ግን እንደማይቃወሙ ተናግረዋል። " ንግግሩን አንቃወምም። ንግግሩን ሂደቱን ለመጀመር በሁለቱም ወገን መስማማት ያስፈልጋል" ብለዋል ፑቲን።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ግን ሩሲያ በርካታ ግዛቶችን ሳትለቅ ተኩስ ማቆም የማይታሰብ ነው ብለዋል።