ሞስኮ ለአፍሪካ ለልማት ስራዎች የሚውል ከ90 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምትመድብ ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል
ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት የ23 ቢሊየን ዶላር የእዳ ስረዛ ማድረጓን ፕሬዝዳንት ቭለድሚር ፑቲን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በሴንት ቢተርስበርግ እየተካሄደ ባለው 2ኛ የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው ሀገራቸው ለአፍሪካ የእዳ ስረዛ ማድረጓን ያስታወቁት።
ፑቲን የእዳ ስረዛው በደፈናው ለአፍሪካ ሀገራት እንደተደረገ እንጂ ለየትኛው ያክል ምን ያክል እዳ ተሰረዘ የሚለው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።
ፑቲን አክለውም ሩሲያ የአፍሪካ ሀገራትን የዕዳ ጫና ለማቃለል በሚደረገው ጥረትም እየተሳተፈች መሆኑን አስታውቀዋል።
ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በቀረበው ጥያቄ መሰረትም ሞስኮ በቅርቡ ለልማት ስራዎች የሚውል 90 ሚሊየን ዶላር እንደምትመድብም ነው ፕሬዳንት ፑቲን ያስታወቁት።
ሩሲያ ለአህጉሪቱ የምግብ አቅራቢ ሆና እንደምትቀጥል ያረጋገጡት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ሞስኮ የምግብ ምርት ለሚያስፈልጋቸው ሀገራት አቅርቦቷን እንምትቀጥልበት አረጋግጠዋል።
- ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ከዶላር ውጪ የንግድ ልውውጥ ክፍያዎችን ታደርጋለች- ፑቲን
- ሩሲያ ኤርትራን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት ለእያንዳንዳቸው ከ25 ሽህ እስከ 50 ሽህ ቶን እህል በነጻ እሰጣለሁ አለች
የሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ የውይይት መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በበኩላቸው ከሩሲያ ጋር ገዘፍ ያለ ወታደራዊ ትብብር ማደረግ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ፑን ትናት በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ከዶላር ውጪ የንግድ ልውውጥ ክፍያዎችን እንምታደርግ ማሳወቃቸው ይታወሳል።
በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 18 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የገለጹት ፐሬዝዳንቱ፤ በቅርብ ጊዜም ጉልህ በሆነ መጠን እድገት እንደሚያስመዘግብም ተናግረዋል።
ለዚህም ሞስኮ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በገንዘብ ልማት ላይ ለመስራት እና የየሀገራን ገንዘቦች ለንግድ ክፍያዎች ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗንም አስታውቀዋል።
በሴንትፒተርስበርግ ከተማ በመካሔድ ላይ በሚገኘው ጉባኤ ከ54 የአፍሪካ አገሮች የ49ኙ ተወካዮች እንደተገኙ ሩሲያ አስታውቃለች። ከእነዚህ መካከል 17 ርዕሳነ-ብሔር እና አራት የመንግሥታት መሪዎች ይገኙበታል።