የአፍሪካ መሪዎች ፑቲን 'የጥቁር ባህር የእህል ስምምነትን' እንዲያድሱ ጫና ማድረጋቸው ተገለጸ
መሪዎች "የአፍሪካ የሰላም ተነሳሽነትችላ ሊባል አይገባም" ብለዋል
የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ለአፍሪካ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል
የአፍሪካ መሪዎች የዩክሬንን ጦርነት ለማቆም ያቀረቡትን የሰላም እቅድ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እንዲወስኑበት ግፊት ማድረጋቸው ተገልጿል።
መሪዎቹ ባለፈው ሳምንት በሞስኮ የተሰረዘውን የጥቁር ባህል የእህል ስምምነት እንዲታደስም ጠይቀዋል።
የአፍሪካ መሪዎች ሩሲያን በቀጥታ ባይተቹም፤ ጦርነቱ በተለይም ለምግብ ዋጋ በማናር ለአፍሪካ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
የኮንጎ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጌሶ ለፑቲን እና ለሌሎች የአፍሪካ መሪዎች በሴንት ፒተርስበርግ "የአፍሪካ (የሰላም) ተነሳሽነት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንጂ ችላ ሊባል አይገባም" ብለዋል።
"በአውሮፓ ውስጥ ሰላም ወደነበረበት እንዲመለስ በድጋሚ እንጠይቃለን" ብለዋል።
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ሩሲያ ባለፈው ሳምንት እድሳት ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ዩክሬን ከባህር ወደቦቿ እህል እንድትልክ የፈቀደችውን የጥቁር ባህርን የእህል ስምምነት እንድታድስ አሳስበዋል።
ሲሲ ሀገራቸው በጥቁር ባህር መስመር የእህል ግዢ ቁልፍ መሆኗን ጠቅሰው፤ "ስምምነት ላይ መድረስ አስፈላጊ" መሆኑን ለጉባኤው ተናግረዋል።
ፑቲን እንደከዚህ ቀደሙ የዓለም የምግብ ዋጋ መናር የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በነበሩት የምዕራባውያን የፖሊሲ ስህተቶች ውጤት ነው በማለት ተከራክረዋል።
ሩሲያ የጥቁር ባህርን ስምምነት የሰረዘችው ምዕራባውያን ስምምነቱ አላከበሩም ብላ ነው።