ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው ፑቲን እምብዛም የውጭ ሀገራት ጉዞ አያደርጉም ነበር
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና በሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቤተ መንግስት ክሬምሊን ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት፤ ፑቲን ከነገ ጀምሮ ነው ጉብኝታቸውን ማድረግ የሚጀምት ተብሏል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ዩሪ ኡሻቭ፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጉብኘታቸውን በሳዑዲ አረቢያ እንደሚጀመሩ እና በዚያም በዚያም ከሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሆመድ ቢን ሰላመ ጋር ይወያያሉ።
በመቀጠልም ወደ አረብ ኢምሬትስ እንደሚያቀኑ እና በዚያም ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አማካሪው አስታውቀዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሁለቱ ሀገራት የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ውይይቶች በጣም ወሳኝ እንደሆነም አማካሪው ዩሪ ኡሻቭ አስታውቀዋል።
የሩሲያው ባለስልጣን የፕሬዝዳንት ፑቲን ጉብኝት መቼ እንደሚጀመር ቁርጥ ያለ ቀን ባያስቀምጡም፤ አል ዐይን ኒውስ ከምንጮች ያገኘው መረጃ ነገ እንደሚጀመር ያመላክታል።
በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና በሳዑዲ አረቢያ በኩል የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ጉብኝት አስመልክቶ እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዓለም አቀፍ የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው በኋላ የውጭ ሀገራት ጉዞን በእጅቁ የቀነሱ ሲሆን፤ አብዛኛውን ጊዜም የቀድሞ የሶቪዬት ህብረት አካል የነበሩ ሀገራትን ብቻ ሲጎበኙ ነበር።
ፑቲን ከእነዚህ ሀገራት ውጪ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ያደረጉት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በቻይና ነበር።