የ2022 የዓለም ዋንጫ ተጠባቂ ጨዋታዎች...
ሳዲዮ ማኔን ያጣችው ሴኔጋል ከኔዘርላንድስ የሚያደርጉት ጨዋታ የዓለም ዋንጫውን ድባብ እንደሚቀይር ይጠበቃል
በፕሪሚየር ሊጉ ከዋክብት የተሞላችው እንግሊዝ ከኢራን የምታደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል
የ2022 የዓለም ዋንጫ አዘጋጇ ኳታር ከኢኳዶር ባደረጉት ጨዋታ ተጀምሯል።
ኳታር በመክፈቻው ጨዋታ የ2 ለ 0 ሽንፈት ብታስተናግድም በሰምንት ስታዲየሞቿ ተጠባቂ ጨዋታዎችን በድምቀት ማስተናገዷን ግን ትቀጥላለች።
በዛሬው እለት በመድብ አየተደለደለችው ሳዲዮ ማኔን ያጣችው ሴኔጋል ከኔዘርላንድስ የሚያደርጉት ጨዋታ የዓለም ዋንጫውን ድባብ እንደሚቀይር ይጠበቃል።
ዛሬ በምድብ 2 የሚደረጉት ጨዋታዎችም የአለም ዋንጫውን ድባብ እንደሚቀይሩ ይጠበቃል።
በተወዳጁ የፕሪሚየር ሊግ ከዋክብት የተሞላችው እንግሊዝ ከኢራን የምታደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ከ64 አመት በኋላ የተመለሰችው ዌልስ አሜሪካን በአህመድ ቢን አሊ ስታዲየም የምትገጥምበት ጨዋታም ልዩ ቦታ ያለው ነው።
የጋሬዝ ሳውዝጌቷ እንግሊዝ በሩስያው የአለም ዋንጫ 4ኛ ሆና አጠናቃለች።
በከዋክብት የተሞላው ቡድን በአለም ዋንጫው በሚጠበቀው ልክ ያለመገኘት የረጅም ጊዜ አባዜ አለበት።
በ1966 በሀገራቸው የተዘጋጀውን የአለም ዋንጫ ካነሱ ወዲህ ስኬት ርቋቸዋል። ሳውዝጌት ከ56 አመት በኋላ ዋንጫ በማንሳት በኢኮኖሚ ድባቴ ውስጥ ያሉ እንግሊዛውያንን እውነተኛ ደስታ ለማጎናፀፍ ተስፋ ሰንቀዋል።
ከ1958ቱ የአለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ በ17 አመቱ ፔሌ ጎል ከውድድሩ ውጭ የሆነችው ዌልስም ከስድስት አስርት በኋላ ያገኘችውን እድል ማባከን አትፈልግም።
የዛሬ ምሽቱን ፍልሚያ ለመመልከት ከ3 ሺህ በላይ የዌልስ ደጋፊዎች ኳታር ገብተው ጨዋታውን እየተጠባበቁ ነው።
አምበሉ ጋሬዝ ቤልም ለሀገራችን ምንም ሳንሰስት ለመስጠትና ድል ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ሲል ተደምጧል።
በርካታ ተጠባቂ ፍልሚያዎችን የሚያስተናግደው ምድብ ሁለት የፖለቲካ ባላንጣዎቹን አሜሪካና ኢራን ያፋጥጣል።
የታላቋ ብሪታንያ ቤተሰቦቹ እንግሊዝና ዌልስ የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።