የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ከምድብ ድልድል እስከ ፍጻሜ ጨዋታ
የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ እለተ ሰኞ ህዳር 12 2015 ዓ.ም ይካሄዳል
የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ታህሳስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም 80 ሺህ ተመልካች በሚይዘው ሉሳይል ስታዲየም ይካሄዳል
የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል፣ መርሐ ግብሮች እና የስታዲየሞችን ትናንት ይፋ አድርጓል።
ትናንት ሌሊቱን ይፋ በተደረገው መርሃ ግብርም የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ እለተ ሰኞ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታውቋል።
የመክፈቻ ጨዋታውም በምድብ አንድ የተደለደሉት አስተናጋጇ ኳታር ከኢኳዶር እንዲሁም የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ሴኔጋል ከኔዘርላንድ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል ተብሏል።
በምድብ ሁለት የተደለደሉት ኢንግላንድ ከኢራን እንዲሁም አሜሪካ፤ የስኮትላንድ፣ ዌልስ አሊያም ዩክሬን አሸናፊ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
በመጀመሪያው የመክፈቻ ቀን ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን በቀን አራት ጨዋታዎች እንደሚካሄዱም ፊፋ አስታውቋል።
ጨዋታዎቹም ቀን 7:00 እና 10:00 ሰዓት እንዲሁም ምሽት 1:00 እና 4:00 ሰዓት ላይ እንደሚካሄዱም ፊፋ በመርሃ ግብሩ አስታውቋል።
የፍጻሜ ጨዋታው ደግሞ ታህሳስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም 80 ሺህ ተመልካች በሚይዘው ሉሳይል ስታዲየም እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።
ፊፋ በትናት ምሽቱ መርሃ ግብሩ የምድብ ድልድልም ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ድልድሉ እንደሚከተለው ቀርቧል፤