እስካሁን ፕሬዝዳንት ባይደን፣ የካናዳ፣ ስዊዘርላንድ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች ከፍተኛ መሪዎች ለንደን ደርሰዋል
የንግስት ኤልሳቤት ስርዓት ቀብር ነገ እንደሚፈጸም ተገለፀ።
ብሪታንያን ላለፉት 70 ዓመታት በንግስትነት ያገለገሉት ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊ በተወለዱ 96 ዓመታቸው በህመም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የንግስቲቱን ሞት ተከትሎም የንግስቲቱ የበኩር ልጁ የሆኑት የ73 ዓመቱ ልጃቸው ልዑል ቻርልስ የብሪታንያ ንጉስ ሆነው ተሹመዋል።
ህይወታቸው ያለፈው የንግስት ኤልሳቤት አሰከሬን ላለፉት 10 ቀናት በተለያዩ የብሪታንያ አደባባዮች እየተዘዋወረ የሀገሪቱ ዜጎችም ሀዘናቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።
በነገው ዕለትም የንግስቲቱ ስርዓተ ቀብር እንደሚፈጸም ቢቢሲ የዘገበ ሲሆን በዚህ ብሄራዊ ስርዓተ ቀብር ፕሮግራም ላይ ከ200 የዓለማችን ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ መሪዎች እና ተወካዮች ይገኛሉም ተብሏል።
በዛሬው ዕለትም በርካታ የዓለማችን መሪዎች ወደ ለንደን በማምራት ላይ ሲሆኑ እስካሁን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ የቻይና ምክትል ፕሬዝዳንት ዋንግ ቂሻን ፣የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ፣ የኒውዝላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን እና ሌሎችም አስቀድመው ለንደን ደርሰዋል ተብሏል።
ብሪታንያ ብሄራዊ የስርዓተ ቀብር ላለፉት 57 ዓመታት ያላዘጋጀቸ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜም የቀድሞውን የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርቺል ሞትን የብሄራዊ ስርዓተ ቀብር ፕሮግራም አሰናድታለች።