በአልጀሪያ የተነሳው ሰደድ እሳት ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ ተሰፋፋ
ባለስልጣናቱ እንደገለጹት የእሳት አደጋ ሰራተኞች አራት አምስተኛ (4/5) የሚሆነውን የእሳት መጠን ማጥፋት ችለዋል
በአልጀሪያ ጎረቤት ቱኒዚያ የሚገኙ አንዳንድ ከሞች 49 ዲግሪ ሴልሼስ ሙቀት አስመዝግበዋል
በሰሜን አፍሪካ የተከሰተውን የሙቀት መጠን መጨመር ተከትሎ በአልጀሪያ የተከሰተው ከባድ ሰደድ እሳት ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ ተዛምቷል።
አልጀሪያ በሜድትራኒያን ባህር በኩል ባለው ግዛቷ የተከሰተውን እና እስካሁን ለ34 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገች መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ባለስልጣናቱ እንደገለጹት የእሳት አደጋ ሰራተኞች አራት አምስተኛ (4/5) የሚሆነውን የእሳት መጠን ማጥፋት ችለዋል።
በከባድ ንፋስ እየተራገበ ባለው እሳቱ ወደ ጎረቤቶ ቱኒዚያ ተስፋፍቷል፤ ሁለት የድንበር መንገዶች እንዲዘጉም አስገድዷል።
በዚህ ወር በቻይና፣ በደቡብ አውሮፖ፣ በአሜሪካ እና በሰሜን አፍሪካ የተከሰተው ክብረወሰን የሰበረ ሙቀት ከባድ ችግር ይዞ መጥቷል።
ግሪክ በሀገሪቱ የተከሰተውን አሳት ለማጥፋት እያደረገች ያለችው ጥረት አንድ ሳምንት ያስቆጠረ ሲሆን በእሳቱ ምክንያት ብዙ ህዝብ እንዲፈናቀል እና የቱሪስት መዳረሻዎቿ እንዲዘጉ ሆኗል።
ባለፈው ሰኞ በበርካታ የአልጀሪያ ቦታዎች የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት 8ሺ ሰው ተሰማርቷል። እሳቱ በተነሳበት ቀጠና የነበሩ 1500 ሰዎች ማዳን መቻሉን ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።
በአልጀሪያ ጎረቤት ቱኒዚያ የሚገኙ አንዳንድ ከሞች 49 ዲግሪ ሴልሼስ ሙቀት አስመዝግበዋል።