የረመዳን እውነታዎች
1445ኛው የረመዳን ጾም በዛሬው እለት ተጀምሯል
እድሜና ጤና ካልገደበ በስተቀር ሁሉም ሙስሊም በረመዳን መጾም ይጠበቅበታል
1445ኛው የረመዳን ጾም በዛሬው እለት ተጀምሯል።
ረመዳን በሂጅራ አቆጣጠር ዘጠነኛው ወር የሚውል ሲሆን በሙስሊሞች ዘንድ የጾምና ጸሎት ወር ነው።
ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ውስጥ አንዱ ሲሆን፤ ጾሙ ለሃያ ዘጠኝ ወይም ሰላሳ ቀናት ይቆያል።
የረመዳን ወር የመረዳዳት፣ የመተጋገዝና የመከባበሪያ ወር ነው።
ሙስሊሙ ማህበረሰብም ፈጣሪ የሚወደውን በጎ ተግባራት በማከናወን ጾሙን እንዲያሳልፍ የእምነቱ አስተምህሮ ያዛል።