ትምህርት እና የጦርነት ጉዳቶች በአማራ ክልል
በአማራ ክልል ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በጦርነቱ ምክንያት ወደ ትምህርት አልገቡም
በክልሉ 298 ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል ወድመዋል ተብሏል
ትምህርት እና የጦርነት ጉዳቶች በአማራ ክልል
ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡
በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ያለው ይህ ጦርነት እየሰፋ መጥቶ አሁን ላይ የአማራ ክልል ሙሉ ለሙሉ በአስቸኳይ አዋጅ እየተዳደረ ሲሆን ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ በክልሉ በተከሰተዉ ጦርነት 298 ትምህርት ቤቶች በከፊል እና ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብለዋል፡፡