የፕሬዝዳንት ትራምት ቀጣይ ክስ እና የታዋቂ አሜሪካውያን ፖለቲከኞች ግብረመልስ
ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው እለት ታህሳስ 08 ቀን 2012 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት እንዲከሰሱ ከተወሰነባቸው ፕሬዘዳንቶች መካካል ሶስተኛ በመሆን በታሪክ ተመዝግበዋል፡፡ ይሁንና በ243 አመት የአሜሪካ ታሪክ በክስ ብቻ ከስልጣን የተነሳ ፕሬዘዳንት የለም፡፡
ፕሬዘዳነቱ ከስልጣን እንዲወገዱ 100 አባላት ካሉት ሴኔት ሁለት ሦስተኛ ድምጽና ቢያንስ 20 የሚሆኑ የሪፐብሊካን አባላት ከዲሞከራቶች ጋር በማበር ከትራምፕ በተቃራኒ መቆም ይኖርባቸዋል፡፡ እስካሁን ባለው ሂደት ግን አንድም የሪፐብሊካን አባል ትራምፕን ተቃውሞ ድምጽ እንደሚስጥ ፍንጭ አላሳየም፡፡
የሴኔት ሪፐብሊካኑ ዋና መሪ ሚች ማክኔል እንደተናገሩት ከሆነ የሪፐብሊካ አባላት ትራምፕን የሚቃወሙበት እድል የለም፡፡ የምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ናንሲ ፖሊሲ ከውሳኔው በኃላ እንደተገሩት ስለሴኔቱ ምርመራ ሂደት እስከሚታወቅ ድረስ የምክር ቤት ኃላፊዎችንና አቃቤያን ህጎችን እንደሚሾሙ ገልጸዋል፡፡
የክሱን አንቀጾች መቼ ወደ ሴኔቱ እንደሚልኩ ግን ግልጽ አላደረጉም፡፡ እሰካሁን ለእኛ ፍትሀዊ የሚመስል ምንምነገር የለም ብለዋል ፖሊሲ፡፡
የምክር ቤቱን ውሳኔ በማስመልከት ከታዋቂ አሜሪካውያን መካከል ጥቂቶቹ ምን አሉ?
በርኔ ሳንድሬስ
የአሜሪካ የቨርሞንት ሴኔትና የዲሞክራት ፕሬዘዳንት እጩ የሆኑት በርኔ ሳንድሬስ ትዊተር ገጻቸው ላይ “ዛሬ አሳዛኝ ቀን ነው፤ ነገር ግን ለአሜሪካ ዲሞከራሲ አስፋላጊ ነው“ ብለዋል፡፡
ሳንድሬስ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ትራምፕን መክሰስ ነበረበት፤ እናም ያደረገው ነገር ትክክለኛ በማለት ከሱን ደግፈዋል፡፡
ሊንድሴይ ግራሃም
የሪፐብሊካን ሴናተርና የፕሬዝዳንት ትራምፕ አጋር የሆኑት ሊንድሴይ ግራሃም በተወካየች ምክር ቤት የጸደቁት የክስ አንቀጾች በሴኔቱ ወድቅ እንደሚሆኑ ግምታቸውን በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡
ፕሬዘዳነቱ ይከሰሱ ከሚለው የዉሳኔ ድምጽ በፊት ሊንድሴይ ግራሃም ”ይህ ምን ማለት ነው፤ ፕሬዘዳንት ትራምፕ በድጋሚ መመረጥ የሚችሉበት ከፍታኛ እድል አለ፡፡“
ሊንድሴይ ግራሃም ከሆነ ክሱ የምርጫ 2013 ጨዋታ አከል ነው ሲሉ ለፕሬዘዳንቱ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋ፡፡
ሚካኤል ብሉምበርግ
የቀድሞው የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባና የዲሞክራቶች የፕሬዘዳንት እጩ ሚካኤል ብሉምበርግ “ምክር ቤቱ በህገ መንግሰቱ ስር ያለውን ኃላፊነት ተወጥቷል፤ እንዳለመታደል ሆኖ ሴኔቱ ግን ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም፡፡“
ምርጫ 2013 ህገመንግስቱን ለመጠበቅ ወይንም ትራምፕ እንዲያቃጥለው የሚፈቅድ ህዝበዉሳኔ እንደሚሆን ሚካኤል ብሉምበርግ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፡-ሮይተርስ