የአሜሪካና አጋሮቿ ተወካዮች የእስያ ፓስፊክ የሚኒስትሮች ስብሰባን ረግጠው ወጡ
የስብሰባው ተካፋዮች ሩሲያን የሚያወግዝ መግለጫ ለማውጣት ማቀዳቸውም ተገልጿል
ተወካዮቹ የሩሲያ ባለስልጣን ንግግር ሲያደርጉ ነው ስብሰባውን ረግጠው የወጡት
የአሜሪካና አጋሮቿ ተወካዮች የእስያ ፓስፊክ የሚኒስትሮች ስብሰባን ረግጠው ወጡ፡፡
ተወካዮቹ የሩሲያ ባለስልጣን ንግግር ሲያደርጉ ነው ስብሰባውን ረግጠው የወጡት፡፡
በታይላንድ መዲና ባንኮክ እየተካሄደ ያለውን የእስያ ፓስፊክ የንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባን ረግጠው የወጡት የካናዳ፣ የኒውዚላንድ፣ የጃፓን፣ የአውስትራሊያ እና የአሜሪካ ተወካዮች ናቸው ተብሏል፡፡
ተወካዮቹ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት የሩሲያ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ንግግር እያደረጉ በነበረበት ሰዓት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሀገራቱ ተወካዮች የሩሲያው ሚኒስትር ንግግር ላይ ሳሉ ስብሰባውን ረግጠው የወጡት ``ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን`` በመቃወም ነው እንደ ዘገባዎች ከሆነ፡፡
ስብሰባውን ረግጠው ወጥተው የነበሩት የአምስቱ ሀገራት ተወካዮች የሩሲያው ሚኒስትር ንግግር አድርገው ሲጨርሱ ተመለሰው መግባታቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የተወካዮቹን ስብሰባውን ረግጦ መውጣት ለሮይተርስ የነገሩት የስበሰባው ተሳታፊ ዲፕሎማቶች ረግጦ ከመውጣት ባለፈ ሩሲያን የሚያወግዝ መግለጫ ሊያወጡ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
ሁለት ቀናትን በሚዘልቀው በዚህ ስብሰባ ላይ የ21 ሀገራት ተወካዮች ይሳተፋሉ፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ሶስት ወራት ሊቆጠሩ ነው፡፡ ሩሲያ በዩክሬን "ልዩ ዘመቻ" እያደረገች መሆኑን ብትገልጽም ምዕራባውያን ግን "ወረራ ነው" በሚል ዘርፈ ብዙ ማዕቀቦችን መጣላቸው ይታወሳል፡፡