ከአደጋው የተረፉት የጠፉባቸውን የቤተሰብ አባላት ለማግኘት በእጆቻቸው ሲቆፍሩ ታይተዋል
በሞሮኮ ከባድ የተባለው ርዕደ መሬት ከተከሰተ ከ48 ሰዓታት በኋላ የነፍስ አድን ሰራተኞች ህይወት ለመታደግ ከጊዜ ጋር እየተሽቀዳደሙ ነው።
በስድስት አስርት ዓመታት ውስጥ እጅግ በጣም ከባድ የተባለው ርዕደ መሬት ከሁለት ሽህ 500 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
የነፍስ አድን ሰራተኛ ከስፔን፣ ብራዚልና ኳታር ፍለጋውን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ አደጋው ከማራኪሽ 74 ኪ.ሜ አቅራቢያ ያለውን ሰሜን ምዕራፍ ክፍል አናውጧል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ከአደጋው የተረፉ አብዛኞቹ ሰዎች ለሦስተኛ ቀን ዶግ አመድ ከሆነው ቤታቸው አቅራቢያ ሜዳ ላይ አድረዋል።
በመሬት መንቀጥቀጡ የተመቱ አካባቢዎችን ለመድረስ አሁንም ከባድ ነው ተብሏል።
የመንገድ መውደምና በፍርራሽ መዘጋጋት በእጅጉ የተጎዱ ስፍራዎች ላይ ለመድረስ ፈታኝ መሆኑ ተሰምቷል።
ከጎርጎሮሳዊያኑ 1900 ወዲህ በጣም ከባድ የተባለው ርዕድ መሬት ሙሉ የጉዳት ሪፖርት እየተጠበቀ ነው።
የሀገሪቱ ሹማምንት በአደጋው የጠፉ ሰዎችን አሀዛዊ መረጃ በሚመለከት እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
ከአደጋው የተረፉ ሰዎች የጠፉባቸውን የቤተሰብ አባላት ለማግኘት በእጆቻቸው ሲቆፍሩ ታይተዋል።
በህይወት የተረፉ ሰዎች መጠለያና ሌሎች ድጋፎችን ባለማግኘታቸው መንግስት ላይ የሰላ ትችት እያቀረቡም ነው።