ፕሬዝዳንት ሪቭሊን የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ዬይር ላፒድ አዲስ ጥምር መንግስትን በቶሎ እንዲመሰርቱ አዘዋል
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጥምር መንግስት ለመመስረት አለመቻላቸውን ተከትሎ ተቃዋሚዎቻቸው ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡፡
ጥምር መንግስት የመመስረት እድሉ በፕሬዝዳንት ሩቨን ሪቭሊን የተሰጠ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ሪቭሊን የየሽ አቲድ ፓርቲ መሪው ዬይር ላፒድ አዲስ ጥምር መንግስትን በቶሎ ሊመሰርቱ የሚችሉበትን እድል መስጠታቸውን ትናንት ረቡዕ ምሽት አስታውቀዋል፡፡
እድሉ በቀጣዮቹ 28 ቀናት ውስጥ ጥምር መንግስት እንዲመሰረት የሚያዝ ነው፡፡
ዬይር ላፒድም ዕድሉን ከዛሬ ከሃሙስ ጀምሮ ለመጠቀምም ከያሚና ፓርቲ ሊቀመንበሩ ናፍታሊ ቤኔት ጋር በመነጋገር ላይ ናቸው፡፡
ሁለቱ የተቃዋሚ መሪዎች ከሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ጥምር መንግስቱን ለመመስረት መፈለጋቸውንም ጀሩሳሌም ፖስት ዘግቧል፡፡
ጥረቱ የሚሳካ ከሆነ ኔታንያሁ በአዲስ ጠቅላይ ሚኒትር የሚተኩ ይሆናል፡፡
ላፒድ እና ናፍታሊም (ከታች በምስሉ ላይ የሚታዩት) በዙር እስራኤልን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያገለግሉ ይሆናል፡፡
እስራኤል ባለፉት 2 ዓመታት አራት ምርጫዎችን አድርጋለች፡፡ ሆኖም በአራቱም መንግስት ለመመስረት አልተቻለም፡፡
የአሁኑ እድል የማይሳካም ከሆነ ለ5ኛ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ የግድ ይላል፡፡