ቤንያሚን ኔታንያሁ ለሀገሪቱ ዜጎች የኮቪድ-19 ክትበትን ማዳረሳቸው ምርጫውን ለማሸነፍ እንደሚረዳቸው ተገምቷል
እስራኤላውያን በሀገሪቱ በ2 ዓመት ውስጥ ለ4ኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለ ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንሁ የፖለቲካ ጉዞ ቀጣይነት ላይ ድምጽ እየሰጡ ነው።
የ71 ዓመቱ ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቱ ዜጎች በፍጥነት የኮቪድ 19 ክትበትን እንዲያገኙ ማድረጋቸው ምርጫውን እንዲያሸንፉ እንደሚረዳቸው ይጠበቃል።
በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ‘ንጉስ ቢቢ’፤ በተቃዋሚዎቻቸው ዘንድ ደግሞ ‘ሙሰኛው ሚኒስትር’ በሚል የሚጠሩት ቤንያሚን ኔታንሁ፤ ከሙስና ጋር ተያይዞ የሚቀርብባቸውን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።
በምርጫ ቅስቀሳ የመጨረሻ ቀናት ላይ በተሰራ ትንብያ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ‘ሊኩዊድ’ ፓርቲ ድጋፍ ከፍ ብሎ መስተዋሉ ተነግሯል።
ትንብያው 120 መቀመጫ ካለው የሀገሪቱ ምክር ቤት ውስጥ 60 መቀመጫውን ኮንሰርቫቲቭ እና አልትራ ኦሮቶዶክስ ጂዊሽ ፓርቲ ጥምረት 60 በመቶ መቀመጫ ሊገኑ እንደሚችልም አመላክቷል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሚመራው ‘ሊኩዊድ’ ፓርቲ እና በተቀያሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒ ጋንዝ ‘ብሉ ኤንድ ኋይት’ ፓርቲዎች መካከል በተፈጠረው ሊታረቅ ያልቻለ የጎላ ልዩነት ምክንያት የእስራኤል ፓርላማ (ክኔሴት) መበተኑ ይታወሳል።
የፓርላማው መበተንን ተከትሎ ነው እስራኤል በ2 ዓመት ውስጥ ለ4ኛ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የተገደደችው።