ክስተቱን የሚያሳየወ ምስል መሰራጨቱን ተከትሎ በርካቶችን አስገርሟል
የሮቦቶች እርስ በርስ እገታ በቻይና
የሮቦቶች ምርት እና ዘመናዊነት እያደገ በመጣበት በዚህ ዓለም ልክ እንደሰው ልጅ እርስ በርሳቸው መጠቃቃት ጀምረዋል ላል ከሰሞኑ ከወደ ቻይና የተሰማው ወሬ፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በቻይና 12 ሮቦቶች በአንድ ድርጅት ውስጥ ያለማቋረጥ ስራቸውን እየሰሩ ነበር፡፡
ድንገት ግን በቻይናዋ ሻንጋይ አንድ አነስተኛ ሮቦት ከየት መጣች ሳትባል በድንገት በስራ ላይ ወደነበሩ ሮቦቶች ክፍል ትገባለች፡፡
ሮቦቷም የትርፍ ሰዓት ስራ እየሰራችሁ ነው? የሚል ጥያቄ በስራ ላይ ለነበሩት ሮቦቶች ታቀርባለች፡፡
ከተጠየቁት ሮቦቶች መካከል አንዱ አዎ የሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን በቃ ከኔ ጋር ኑ ተከተሉኝ ብላ ወደ መጣችበት ስትመለስ 10ሩ ሮቦቶች የተባሉትን እንዳደረጉ በክፍሉ ውስጥ ተገጥሞ የነበረው ካሜራ ያስቀረው ምስል ያስረዳል፡፡
መጀመሪያ ላይ የተለመደ የሚመስለው ይህ ቪዲዮ ግን ባለንብረቱ ሮቦቶቼ ባልታወቀ ሮቦት ታግተው ተወሰዱብኝ የሚል መግለጫን ካወጣ በኋላ ጉዳዩ የበርካቶችን ትኩረት ስቧል፡፡
በተለይም የሮቦቶቹ እርስ በርስ የቃል ልውውጥ ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን እኛ እኮ እረፍት የለንም፣ ቤትም የለንም ወዴት መሄድ እንችላለን እና የመሳሰሉት ሀሳቦች አስገርመዋል፡፡
በጸና የታመሙ ተማሪዎችን ተክቶ ክፍል ውስጥ የሚገባው ሮቦት
የሮቦቶ አምራች ኩባንያው ሀንግዙ ኩባንያ ክስተቱ እውነት መሆኑን የገለጸ ሲሆን ቆይቶ በወጣ መረጃ ደግሞ ሮቦቶች እርስ በርስ መጎዳዳት መቻል አለመቻላቸውን ለመለየት በሚል የተደረገ እንደሆነ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በተለይም እገታውን ፈጽማለች የተባለችው አነስተኛ ሮቦት የሌሎቹን ሮቦቶች ስሪት እንድታውቅ መደረጓንም አምራቾቹ ገልጸዋል፡፡