ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለሳኡዲው ክለብ አል ናስር የመጀመሪያውን ሃት-ትሪክ አስቆጥሯል
ሮናልዶ በ21ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት የመጀመሪያ ጎል 500ኛ የሊግ ጎል ሆኗ ተመዝግባለታለች
ሮናልዶ ሃት-ትሪክ ሲሰራ በእግር ኳስ ህይወቱ ለ61ኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለሳኡዲው ክለብ አል ናስር የመጀመሪያውን ሃት-ትሪክ አስቆጥሯል፡፡
ከቀናት በፊት 38ኛ ልደቱን ያከበረው ሮናልዶ ሃት-ትሪክ መስራት የቻለው ክለቡ አል-ናስር ከአል-ዌህዳ ጋር በነበረው ጨዋታ ነው፡፡
ሮናልዶ በ21ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ጎል በግራ እግሩ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ጎሏ በሮናልዶ የእግር ኳስ ህይወት 500ኛ የሊግ ጎል ሆኗ ተመዝግባለታለች፡፡
ሮናልዶ ከእረፍት በፊት ሌላ በአስደናቂ አጨራረስ ያስቀጠራት ሌላኛዋ ጎል ክለቡ 2 ለ0 በሆነ ውጤት እየመራ እረፍት እንዲወጣ ያስቻለችም ነበረች፡፡
በተጨማሪም በሁለተኛው አጋማሽ በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠር ክለቡ 3 ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሎታል፡፡
አል-ናስሮች ወደ አል-ዌህዳ የተጓዙት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪያቸውን ታሊስካ ሳያካትቱ የነበረ ቢሆንም፤ ሮናልዶ ብራዚላዊውን የግብ አዳኝ በመተካት አራት ጎሎችን ማስቆጠር እንደሚችል ያረጋገጠበት ጨዋታ ሆኖ አልፏል፡፡
ሮናልዶ ክለቡ ከአል-ዌሃድ ጋር በነበረው ጨዋታ ያስቆጠራቸው አራት ጎሎች አል-ናስር ወደ ሳኡዲ ፕሮፌሽናል ሊግ መሪነት እንዲመለስ ያስቻሉም ነበሩ፡፡
የቀድሞው የሪያል ማድሪድ እና የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጫዋች ሮናልዶ ሃት-ትሪክ ሲሰራ በእግር ኳስ ህይወቱ ለ61ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
ሮናልዶ በጨዋታው ያስቆጠራቸው ጎሎች ተጨዋቹ እድሜው ቢገፋም አሁንም በድንቅ ብቃት ላይ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ተብሏል፡፡
በተጨዋሪም ፖርቹጋላዊው ኮከብ በአንድ ጨዋታ አራት ጎሎችን ሲያስቀጥርም ከአራት አመታት በኋላ መሆኑ ነው፡፡
ሮናልዶ እንደፈረንጆቹ በ2019 ፖርቹጋል ከሜዳው ውጪ ሊትዌኒያን 5-1 ስያሸነፍ አራት ጎሎች አስቆጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡