የሳኡዲው ክለብ አል ናስር ለሽንፈቱ ፖርቹጋለዊውን ኮከብ ሮናልዶን ተጠያቂ አደረገ
የትናንቱ ጨዋታ ለሮናልዶም ሆነ ለክለቡ አል-ናስር አሳዛኝ ሽንፈት ነው ተብሏል
የአል-ናስር ስራ አስኪጅ ሩዲ ጋርሺያ፤ ሮናልዶ እድሎችን አለመጠቀም ክለቡን ዋጋ አስከፍሎታል ብለዋል
ሐሙስ ምሽት በነበረው የሱፐር ካፕ የግማሽ ፍታሜ ጨዋታ አል-ናስር በአል-ኢትሃድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸብፏል።
ቢዘህም አል-ናስር ከሱፐር ካፕ ውድድር ውጭ የሆነ ሲሆን ለደረሰበት ሽንፈት ክለቡ በቅርቡ የተቀላቀለውን ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን ተጠያቂ አድርጓል።
የአል-ናስር ስራ አስኪጅ ሩዲ ጋርሺያ ሮናልዶ በመጀመሪያው አጋማሽ የተፈጠሩትን እድሎች ተጠቅሞ ኳስና መረብ ማገናኘት አለመቻሉ ቡድኑን ዋጋ አስከፍሎታል ብለዋል።
የሮናልዶ እድሎችን አለመጠቀም “የጨዋታውን ሂደት ቀይሯል” ሲሉም ነው የተናገሩት ስራ አስኪያጁ።
እንደ ጎል-ስፖርት ዘገባ ከሆነ የትናንቱ ምሽት ጨዋታ ለሮናልዶም ሆነ አል-ናሰር ክለብ የማይረሳና አሳዛኝ ሽነፈት ሆኖ አልፏል።
ከአሁኑ ትችት ማስተናገድ የጀመረው የቀድሞው ማንቸስተር ዩናይትድ ኮከብ በሳኡዲ ፕሮፌሽናል ሊግ ክለቡ በሚቀጥለው አርብ ከአል ፋቲህ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ጎል ያስቆጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከማን ዩናይትድ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ኦልድ ትራፎርድን ለቆ በ200 ሚሊዮን ዶላር አል-ናስርን የተቀላቀለው ሮናልዶ በሳኡዲ ፕሮፌሽናል ሊግ ትልቅ መነቃቃት እንደፈጠረ ይገለጻል።
ሮናልዶም ቢሆነ በአውሮፓ ያገኘውን ስኬትና ልምድ በእስያ ማጋራት እንደሚፈልግ ሲናገር ይደመጣል።
ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ጠቢብ አምስት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ከማንሳት በዘለለ በእንግሊዝ፣ በስፔን እና ጣሊያን ሰባት የሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለ ድንቅ ተጨዋች ነው።
በአምስት የዓለም ዋንጫዎች የተሳተፈና ጎል በማስቆጠር ታሪክ የሰራም ነው ሮናልዶ።
እናም “ሮናልዶ በአል-ናስር ቆይታው ይህ ደማቅ ታሪክ ያስቀጥለው ይሆን?“ የሚለው ሁንም በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁት ጎዳይ ነው።