ሩኒ ከሳኡዲ አረቢያ የቀረበለትን ጥያቄ አለመቀበሉን ተናገረ
ሩኒ ያሳለፈው ውሳኔ ወደ ሳኡዲ እንዲሄድ የፈለጉትን ስራ አስኪያጆች "ያለማክበር አይደለም" ብሏል
ዋይኒ ሩኒ የእንግሊዙን በርሚንግሃም ሲቲን ለማስልጠን ከመምረጡ በፊት ከሳኡዲ ፕሮ ሊግ ቀርቦለት የነበረውን ጥያቄ ሳይቀበለው መቅረቱን ተናግሯል
ዋይኒ ሩኒ ሁለተኛ ዲቪዤን ላይ ያለውን የእንግሊዙን በርሚንግሃም ሲቲን ለማስልጠን ከመምረጡ በፊት ከሳኡዲ ፕሮ ሊግ ቀርቦለት የነበረውን ጥያቄ ሳይቀበለው መቅረቱን ተናግሯል።
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ እና የእንግሊዝ አጥቂ እንዲሁም ቀደም ሲል የዲሲ ዩናይትድ እና የደርቢ ካውንቲ አሰልጣኝ የነበረው ሩኒ በሻምፒዮንሺፕ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ያለውን በርሚንግሃምን ለማሰልጠን ባለፈው ሮብዕ እለት ቅጥር ፈጽሟል።
የበርሚንግሃም ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋሪ ኩክ ሩኒ የሳኡዲ አረቢያ ፕሮ ሊግ ኃላፊ ሆኖ እንዲሄድ መሞከሩን ተናግሯል።
"የሳኡዲ አረቢያን ጉዳይ ተወያይናል። ግን ሊሆን አልቻለም"ሲል ኩክ ከሩኒ ጋር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል።
ሩኒ ወደ ሳኡዲ አቅንቶ ቢሆን ኖሮ የቀድሞ የእንግሊዝ ቡድን አጋሩ የነበረውን እና ባለፈው ሀምሌ ወር የአል ኢቲፋቅ ስራ አስኪያጅ ሆኖ የተቀጠረውን ስቴቨን ጀራርድን ይቀላቀል ነበር።
ሩኒ ያሳለፈው ውሳኔ ወደ ሳኡዲ እንዲሄድ የፈለጉትን ስራ አስኪያጆች "ያለማክበር አይደለም" ብሏል።
"ለእኔ መጀመሪያ ወደ እንግሊዝ እግርኳስ መመለሴ ትልቅ ነገር ነው። ይህን ነው መስራት የምፈልገው። ባለፉት አራት እና ስድስት አመታት ውስጥ በርካታ እድሎች አጋጥመውኝ ነበር። ነገርግን በርሚንግሃምን ለመቀላቀል ቀላል ውሳኔ አሳልፌያለሁ" ሲል ተናግሯል ሩኒ።
ሩኒ አክሎም እንደገለጸው "ስኬታማ መሆን እፈልጋለሁ፤ ይህ ክለብም ስኬታማ መሆን ይፈልጋል። ሁላችንም የተነጋገርነው ተመሰሳይ ነው"።
ሩኒ በክለቡ ኃላፊነት ከያዘ በኋላ በርሚንግሃም በፈረንጆቹ ጥቅምት 21 ሚድልስቦሮው ጋር ይጫወታል።