የሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ ለተጨዋቾች ግዥ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አደረገ
በቅርቡ ስሙ የገነነው የሳኡዲ ፕሮሊግ የበርካታ የአውሮፖ ሊግ ታዋቂ ተጨዋቾች መዳረሻ እየሆነ መጥቷል
አዲስ የእግር ኳስ መናኸሪያ መሆኗን ያስታወቀችው የነዳጅ ባለጸጋዋ ሳኡዲ አረቢያ ትናንት በባቃው የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት 1 ቢሊዮን ዶላር አወጣች
የሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ ለተጨዋቾች ግዥ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አደረገ
የዘንድሮው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲዘጋ የሳኡዲ አረቢያው ፕሮሊግ 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አውጥቷል።
አዲስ የእግር ኳስ መናኸሪያ መሆኗን ያስታወቀችው የነዳጅ ባለጸጋዋ ሳኡዲ አረቢያ ትናንት በባቃው የተጨዋቾች ዝውውር 1 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን ኤፒ ዘግቧል።
ኮከቡ መሀመድ ሳላህ ክርስቲያኖችን ሮናልዶን ባይቀላቀልም፣ ካሪም ቤንዜማ እና ኔይማር የተቀላቀሉበት የሳኡዲ ፕሮሊግ ቡዙ ኮከብ ተጨዋቾችን ከአውሮፖ ሊግ ማስኮብለሉ የማይቀር እንደሆነ እየተነገረ ነው።
ባለፈው ሳምንት ሊቨርፑል የሳኡዲው አሊ-ትሃድ መሀመድ ሳለህን ለማስፈረም 188 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦለት የነበረ ቢሆንም ክለቡ ውድቅ አድርጎታል።
በትናንትናው እለት የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ክለቡ እንደገና ሌላ ዋጋ ማቅረቡን
የሚገልጹ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም ግብጻዊውን አለምአቀፍ ተጨዋች ለማስፈረም ስምምነት አልተደረሰም።
በቅርቡ ስሙ የገነነው የሳኡዲ ፕሮሊግ በበርካታ የአውሮፖ ሊግ ታዋቂ ተጨዋቾች መዳረሻ እየሆነ መጥቷል።
ሳኡዲ አረቢያ እግር ኳስን ጨምሮ በጎልፍ፣ በቦክስ፣ ፎርሙላ ዋን ሬሲንግ እና በቴኒስ ላይ ኢንቨስት እያደረገች።
ፕሮሊግ በተጠናቀቀው የዝወውር መስኮት ያለወጣው ወጭ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ካወጫው ወጭ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።