ሩሲያ፤ ዩክሬንን በዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ጣቢያ አዲስ ተኩስ ከፍታለች ስትል ከሰሰች
ሩሲያ እና ዩክሬን በኒውክሌር ጣቢያው ላይ ጉዳት በማድረስ እርስበእርሳቸው እየተካሰሱ ነው
ሩሲያ የተመድ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ቡድን ምርመራ ለማድረግ ወደ ስፍራው እንዲሄድ ሩሲያ ፈቅዳለች
በዩክሬን ኢነርሆዳር ውስጥ በሩሲያ የተሾሙ ባለስልጣናት የዩክሬን ወታደሮች እንደገና በዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል የሚል ክስ አቅርበዋል፡፡
ሮይተርስ የሩሲያውን ዜና ወኪል ታስን ጠቅሶ እንደዘገበው ዩክሬን እንደ አዲስ ጥቃት ፈጸማለች የሚል ክስ በሩሲያ ቀርቦባታል፡፡
የከተማዋ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ሁለት ተኩሶች በፋብሪካው የነዳጅ ማከማቻ ህንፃ አጠገብ ፈንድተዋል ሲል ኤጀንሲው አክሎ ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ቡድን በዩክሬን ወደ ሚገኘውና በሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ወዳለው ዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ጣቢያ አቅንቷል፡፡
ዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ጣቢያ በጦርነቱ ምክንያት በአከባቢው ላይ መጠነ ሰፊ የተኩስ ልውጦች እየተካሄዱ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ በኒውክሌር ጣቢያው ላይ ጥቃት ከደረሰ የጨረር አደጋ እንዳያስከትል በርካቶች ስጋታቸው ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
ሩሲያ እና ከዩክሬን ከአውሮፓ ትልቅ የሆነውን እና በዩክሬን የሚገኘውን የኑክሊየር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ጥቃት በማድረስ እርስ በእርሳቸው በመካሰስ ላይ ባሉበት ወቅት ተመድ ከጦር ነጻ ቀጣና እንዲቋቋም ሀሳብ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በደቡባዊ ዩክሬን የሚገኘው እና ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” እንደጀመረች በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር የዋለው የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጥቃት ደርሶበታል ተብሏል፡፡