ፖለቲካ
ሩሲያ ምዕራባውያን የዩክሬኑን ጦርነት ወደ እስያ-ፖሲፊክ ማስፋፋት ይፈልጋሉ ስትል ከሰሰች
ሾይጉ እንዳሉት ኔቶ በቀጣናው የሚያደርገውን ወታደራዊ ልምምድ መጠን እና ድግግሞሽ ጨምሯል
ሾይጉ በቻይና በተካሄደ ትልቅ ወታደራዊ ፕሮግራም ላይ ኔቶ በእስያ-ፖሲፊክ ቀጣና ወታደራዊ ኃይል እየገነባ ነው ብለዋል
ሩሲያ ምዕራባውያን የዩክሬኑን ጦርነት ወደ እስያ-ፖሲፊክ ማስፋፋት ይፈልጋሉ ስትል ከሰሰች።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ምዕራባውያን የዩክሬኑን ጦርነት ወደ እስያ-ፖሲፊክ ለማስፋፋት ፍላጎት አላቸው ሲሉ ከሰዋል።
ሾይጉ በቻይና በተካሄደ ትልቅ ወታደራዊ ፕሮግራም ላይ ኔቶ በእስያ-ፖሲፊክ ቀጣና ወታደራዊ ኃይል እየገነባ ነው ብለዋል።
የኔቶ ሀገራት በቀጣና የወታደራዊ አቅም ግንባታን በማበረታት ያለቸውን ሚና ለመጨመር እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋ።
ሾይጉ እንዳሉት ኔቶ በቀጣናው የሚያደርገውን ወታደራዊ ልምምድ መጠን እና ድግግሞሽ ጨምሯል።
የአሜሪካ ኃይሎች ከጃፖን እና ደቡብ ኮሪያ ጋር በሚሳይል ማስወንጨፍ ዙሪያ መረጃ በመቀያየር ሩሲያ እና ቻይናን ለማስፈራራት እየሰሩ ናቸው ብለዋል ሾይጉ።
ሾይጉ አክለውም አሜሪካ የአየር ንብረት ለውጥን እና የተፈጥሮ አደጋን "ለጣልቃገብነት" እንደ ሰበብ ትጠቀማለች የሚል ክስም አቅርበዋል።