ሩሲያ የሀማስ ግብዣ በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ውስጥ ያሉትን ሁሉንም አካላት የማነጋገር ጥረት አካል ብላለች።
እስራኤል ተቃውሞዋን ለመግለጽ የሩሲያን አምባሳደር ጠራች።
ሞሰኮ የሀማስን የልኡካን ቡድን በመጋበዟ የተቆጣችው እስራኤል ተቃውሞዋን ለመግለጽ የሩሲያን አምባሳደር አናቶሊ ቪክቶሮቭ ጠርታለች።
- በእስራኤል የአየር ድብደባ 47 መስጊዶችና 7 ቤተ ክርስቲያኖች ወድመዋል ተባለ
- ወደ ሁለተኛው ምእራፍ ተሸጋግሯል በተባለው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት የተፈጠሩ አዳዲስ ክስተቶች ምንድናቸው?
እስራኤል በጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ባደረሰው ከባድ ጥቃት 1400 ዜጎቿን የገደለው የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ እንዴት ሞስኮን ይጎበኛል የሚል ቁጣ አሰምታ ነበር።
እስራአል አምባሳደሩን የጠራችው ይህንኑ ቅሬታዋን ለማሰማት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሀማስን መጋበዝ ማለት ሽብርተኝነትን በእስራኤል ላይ ህጋዊ የማድረግ መልእክት ያስተላልፋል" ብሏል የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ።
ሚኒስቴሩ ጥሪው የተቃውሞ እንጂ የማስጠንቀቂያ አይደለም ብሏል።
ሩሲያ በአንጻሩ የሀማስ ግብዣ በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ውስጥ ያሉትን ሁሉንም አካላት የማነጋገር ጥረት አካል ብላለች።
ሩሲያ በሀማስ እና በእስራኤል መካከል ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ ካቀረቡት ሀራት መካከል ነች።
የሀማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል እየወሰደች ያለውን የአጸፋ እርምጃም ሩሲያ ተችታዋለች።
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለው ድብደባ አለምአቀፍ ህግን የሚጥስን ለአስርት አመታት የሚዘልቅ የሚተረፍ ችግሮ ያስከትላል ብለዋል።
ሩሲያ ሽብርተኝነትን በግልጽ የምታወግዝ ቢሆኖም በሽብርተኞች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ንጹሃንን ያለየ መሆኑ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
ሀማስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የዛተችው እስራኤል ጋዛን በመክበብ በእግረኛ ወታደር ወረራ ጥቃት ከፍታለች።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢወስንም፣ እስራኤል አሻፈረኝ ብላ ማጥቃቷን ቀጥላቀታለች።