ፖለቲካ
ሩሲያ ከዩክሬን ወደ ግዛቷ ለጠቀለለቻቸው አራት ግዛቶች ልማት 20 ቢሊዮን ዶላር መደበች
በምዕራባውያን የምትደገፈው ዩክሬን እና ሩሲያ እያደረጉት ያለው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው
ፑቲን ግዛቶቹን ወደ ሩሲያ ባጠቃለሉበት ወቅት እንደተናገሩት በአራቱ ግዛቶች ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል
ሩሲያ ባለፈው አመት ወደ ግዛቷ ላካተተቻቸው አራት ግዛቶች ልማት የሚውል 20 ቢሊዮን ዶላር መድባለች።
ፕሬዝደንት ፑቲን እንደገለጹት ሩሲያ በሚቀጥሉት ሁለት ከግማሽ አመታት በሚሆን ጊዜ ውስጥ በግዛቶቹ ለሚተገበር ልማት ከፌደራል በጀት 20 ቢሊዮን ዶላር ይመደባል ብለዋል።
ሩሲያ ሀሉንም ግዛቶች መሉ በሙሉ ያልተቆጣጠረች ሲሆን ባለፈው አመት ግዛቶቹን ለመጠቅለል ያሳለፈችው ውሳኔም በተለይም ከምዕራባውያን ውግዘትን አስከትሎባታል።
ፑቲን ግዛቶቹን ወደ ሩሲያ ባጠቃለሉበት ወቅት እንደተናገሩት በአራቱ ግዛቶች ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት በሩሲያ ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል።
ሩሲያ ኬርሶን፣ ዛፖሬዥያ፣ ዶምባስ እና ሉሀንስክ ግዛት ወደ ግዛቷ የጠቀለለችው በህዝበ ውሳኔ ነው ብትልም ዩክሬን እና ምዕራባውያን የሀሰት ህዝበ ውሳኔ ነው ብለውታል።
በምዕራባውያን የምትደገፈው ዩክሬን እና ሩሲያ እያደረጉት ያለው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።