ሰይጣን' የተሰኘው እና ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው የሩሲያው ሳርማት-2 ሚሳይል'
ይህ መሳሪያ በመሬት ላይ በየትኛው እርቀት ላይ ያለ ኢላማን መምታት እንደሚችልም ተገልጿል
የምዕራባውያኑ ወታደራዊ ጥምረት ወይም ኔቶ 'ዴቪል' ሲል የጠራው ይህ የሩሲያ ሚሳይል በዓለም ኃይለኛ የሚባል መሳሪያ ነው ተብሏል
ሩሲያ 'ሰይጣን' የተሰኘውን ሳርማት-2 ሚሳይል ጥቅም ላይ አውላለች።
የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት ወይም ኔቶ 'ዴቪል' ሲል የጠራው ይህ የሩሲያ ሚሳይል በዓለም ኃይለኛ የሚባል መሳሪያ ነው ተብሏል።
ይህ መሳሪያ በመሬት ላይ በየትኛው እርቀት ላይ ያለ ኢላማን መምታት እንደሚችልም ተገልጿል።
ሳርማት ሩሲያ በቅርብ አመታት ያበለጸገችው ስትራቴጅክ ኢንተርኮንቲኔንታል ባለስቲክ ሚሳይል ነው።
በዛሬው እለት የሮስኮሶሞስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዩሪ ቦሪሶቭ ይህ ሚሳይል ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ሳርማት አቅም ምን ያህል ነው?
ሳርማት በቅሩቡ በሩሲያ የተሰራ ኢንተርኮንቲኔታል ሚሳይለ ሲሆን በመሬት ላይ በየትኛው እርቀት ላይ ያለ ኢላማን ይመታል ተብሏል።
ሚሳይሉ 200 ቶን ክብደት ያለው ሲሆን እያንዳንዱ ሚሳይል ከ10 ተተኳሽ ጋር መንቀሳቀስ ይችላል ተብሏል።
ሚሳይሉ ከጸረ-ሚሳይል መከላከያ ስርአት እንዲደበቅ ሆኖ የተሰራ መሆኑ ለየት ያደርገዋል። ይህ ሚሳይል በሰአት 24ሺ ኪሎሜትር የሚጓዝ ሲሆን ይህም ከድምጽ 20 እጥፍ የሚበልጥ ነው።
የሳርማት-2 የጦር መሳሪያን ጥቅም ላይ መዋል ይፋ ያደረገችው ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት የጀመረችውን የዩክሬን ጦርነት በአዲስ መልኩ ልትጀምር ይመስላል።