ሩሲያ በክህደት የጠረጠረችውን የሳይበር-ሴኩሪቲ ከፍተኛ ኃላፊ አሰረች
ሩሲያ የሳይበር-ሴኩሪቲ ኃላፊውን የሩስያ ሚስጥራዊ ሰነዶች ለውጭ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ነው
ተጠርጣሪው ወንጀለኛ ሆኖ ከተገኘ በሩስያ ህግ መሰረት እስከ 20 ዓመት የእስር ቅጣት የሚበየንበት ይሆናል
ሩሲያ በክህደት የጠረጠረችውንና ከሀገሪቱ የደህንነት ተቋማት አንዱ የሆነውን የሳይበር ግሩፕ-ኣይቢ ኃላፊ አሰረች፡፡
የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንጀሉ የተጠረጠረውን ከፍተኛ የሳይበር ሴኩሩቲ ኃላፊ ኢልያ ሳችኮቭን ለሁለት ወራት በእሰር እንዲቆይ ያዘዘ ቢሆንም በክሶቹ ዝርዝር ላይ እሰካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
ይሁን እንጅ የ35 ዓመቱ ኢልያ ሳችኮቭ የሩስያ ሚስጥራዊ ሰነዶች ለውጭ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ሳይከሰስ እንዳልቀረ ከምንጮቼ ሰምቻለሁ ሲል ሮይተረስ ዘግቧል፡፡ ሳችኮቭ ለደህንነት ተቋማት አሳልፎ የሰጠው ሰነድ እንደሌለ ተገልጿል፡፡
ሳችኮቭ የሚመራው የግሩፕ-አይቢ ተቋም የሳይበር ጥቃትን በመከላከል የሚሰራ ሲሆን፤ እንደ ኢንትርፖል የመሳሰሉ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ደምበኞቹ ናቸው፡፡
ምክንያቱ ባይገለጽም የተቋሙ የሞስኮ እና የሰንት ፒተርስበርግ ጽ/ቤቶች መፈተሻቸው አርአይኤ የተሸኘ የዜና ወኪል ገልጸዋል፡፡
የቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ ዲመትሪ ፐስኮቭ ፤የክሬምሊን ቤተመንግስት ስለ ክሱ የሚያውቀው ነገር የለም ሲል ተደምጠዋል፡፡
ሳችኮቭ፡ በወንጀል መጠርጠሩን ተከትሎ በቅርቡ በሩስያ በክህደት ከተከሰሱ የሳይበር -ሴኩሪቲ ባለሙያዎች እና ጋዜጠኖች አንዱ ሆኗል፡፡፡ተጠርጣሪው ወንጀለኛ ሆኖ ከተገኘ በሩስያ ህግ መሰረት እስከ 20 ዓመት የእስር ቅጣት የሚበየንበት ይሆናል፡፡
ሳችኮቭ በ17 ዓመቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን ግሩፕ-አይቢ ን የመሰረተ ሲሆን ፤ እንደፈረንጆቹ በ2016 2016 ‘‘ከ30 የእድሜ ክልል በታች ከሆኑ 30 በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ፈጣሪዎች’’ አንዱ በሚል በፎርብስ መጽሄት መመረጡ የሚታወስ ነው፡፡
ፎርብስ ሳችኮቭ የሳበር ወንጀሎችን ለማጋለጥ በሚል ከባንኮች፣ የሩሲያ የሀገር ውስጥ ደህንነት እና ኢንትርፖል ይሰራ እንደነበርም በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡
ከሶስት ዓመታት በኋላም የኮምፒዩተር ሲስትም አዳጋዎች በማስተዋወቅና በመከላከል ረገድ በሰራው ስራ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሽልማት ተብርክቶለት ነበር፡፡
በአንጻሩ ሩሲያ በምዕራቡ ዓለም ሀገራት ላይ የሳይበር ጥቃት ፈጽማለች የሚል ክስ እቀረበላት ቢሆኑም ክሶቹ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል ውድቅ ስታደርግ ይስተዋላል፡፡