ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመሩ ሶስት ወር ሞላ
የሩሲያ ኩባንያዎች ምርታቸውን ሲሸጡ 50 በመቶውን ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንዲያደርጉ ተወሰነላቸው፡፡
የሀገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስቴር፤ ቀደም ሲል ኩባንያዎች ከሚያከናውት ሽያጭ 80 በመቶውን በውጭ ምንዛሬ እንዲያከናውኑ የተጣለው መመሪያ ማሻሻያ መደረጉን ገልጿል።
ከዚህ በፊት ሞስኮ ኩባንያዎቿ ከሚሸጡት ምርት ላይ 80 በመቶው የሚሆነውን በውጭ ምንዛሬ እንዲሆን ወስና ነበር።
ይሁንና አሁን ላይ የሩሲያ የመገበያያ ገንዘብ ሩብል የተረጋጋ ምንዛሬ ላይ ስላለ ቅናሽ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።
ሩሲያ ኩባንያዎቿ 80 በመቶ የሚሆነውን ሽያጫቸውን በውጭ ምንዛሬ እንዲደረግ ወስና የነበረው ምዕራባውያን የጣሉባትን ማዕቀብ ተከትሎ እንደነበር ተገልጿል።
አሁን ላይ ሩብል ከሌሎች ሀገራት ገንዘብ ጋር ያለው ምንዛሬ የተረጋጋ መሆኑንም ሩሲያ ገልጻለች። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ የሩሲያ ኢኮኖሚ ከምዕራቡ ዓለም የተጣለውን የማዕቀብ ውርጅብኝ መቋቋሙን ገልጸዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ወታደራዊ ዘመቻ” እንዳደረገች ከገለጸች እንዲሁም ምዕራባውያን እንደሚሉት በዩክሬን ላይ ወረራ ካካሄደች ዛሬ ሶስተኛው ወር ገብቷል።