'ድሬል' ከ14 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ተለቆ ወደ 50 ኪሎሜትር በአየር ላይ ወደ ጉን መሄድ ይችላል ተብሏል
ሩሲያ በ2024 በከፍተኛ ቁጥር ለማምረት ያቀደችው መሳሪያ ምንድነው?
ሩሲያ በፈረንጆቹ 2024 ክላስተር 'ድሬል' የተሰኘ ቦምብ በከፍተኛ ቁጥር ልታመርት ነው ተባለ።
በምዕራባውያን ከምትደገፈው ዩክሬን ጋር እየተዋጋች ያለችው ሩሲያ፣ የጦር መሳሪያ ምርቷን እንደምትጨምር መግለጿ ይታወሳል።
ታስ የተባለው የሩሲያ ሚዲያ የሩሲያውን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሮዝቴክ ጠቅሶ እንደዘገበው የድሬል ቦምብ የመጀመሪያው ባች በዚህ አመት ይመረታል።
ምርቱ ሁሉንም አይነት ሙከራዎች ማለፉን የገለጸው ሮዝቴክ ተተኳሾቹ በመሰራት ላይ ናቸው ብሏል።
የድሬል ቦምብን በከፍተኛ ቁጥር የማምረት እቅድ፣ 10ሺ ገደማ ኤስ-8ኬኤል የተሰኘ 'ጋይድድ ክላስተር አቬሽን ሙኒሽን' መመረቱን ተከትሎ የመጣ ነው።
ይህ ቦምብ የተሰራው በ2016 ሲሆን ሙከራ እና ግምገማው ያለቀው ግን በ2023 ነው።
ክብደቱ 540 ኪሎግራም ይመዝናል የተባለው ይህ ቦምብ፣ ራሳቸውን ችለው እተፈለገበት ርቀት ድረስ የሚበሩ እና የሚፈነዱ 15 ንዑስ ፈንጅዎች አሉት ተብሏል።
ዘገባው እንደጠቀሰው ከሆነ ቦምቡ በተቀመጠለት ጊዜ የማይፈነዳ ከሆነ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ራሱን ማክሸፍ ይችላል።
ከዚህ በተጨማሪም ቦንቡን ከርቀት መቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ ተገጥሞለታል።
ይህ ቦምብ ከ14 ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ተለቆ 50 ኪሎሜትር በአየር ላይ ወደ ጉን መሄድ ይችላል ተብሏል።
ቦምቡ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን፣ የራዳር ጣቢያዎችን፣ የኃይል መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን እና የጸረ-አውሮፕላን ሚሳይል ሲስተሞችን ለማውደም እንዲያስችል ሆኖ የተሰራ ነው።