በጦር መሳሪያ ምርት እሽቅድምድም ሩሲያ ምዕራባውያንን የመምራት አቅም እንዳላት ገለጸች
ዩክሬን እና ምዕራባውያን አጋሮቿ በዩክሬን የውጊያ አውዶች ላይ የሩሲያ ኃይሎችን ለማሸነፍ የጦር መሳሪያ ምርታቸውን ጨምረዋል
አንዳንድ የቀድሞ መሪዎች የሩሲያ 2.2 ትሪሊየን ዶላር የምዕራባውያንን ግዙፍ አቅም መቋቋም አይችልም እያሉ ናቸው
በጦር መሳሪያ ምርት እሽቅድምድም ሩሲያ ምዕራባውያንን የመምራት አቅም አለኝ አለች።
ሩሲያ የጦር መሳሪያ በማምረት ከምዕራባውያን የተሻለች መሆኗን እና የምርት ምጥነቱንም ከፍ እንደምታደርገው አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ሩሲያ እና ምዕራባውያን ለዩክሬን ጦርነት የሚሆን የጦር መሳሪያ ምርት መጨመራቸውን ተከትሎ ነው።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ በፈረንጆቹ 2022 መክፈቷ ከሁለተኛ የአለም ጦርነት እና ከቀዝቃዛው ጦርነት የሩሲያ እና ምዕራባውያን ፍጥጫ በኋላ በአውሮፖ ትልቅ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን አጋሮቿ በዩክሬን የውጊያ አውዶች ላይ የሩሲያ ኃይሎችን ለማሸነፍ የጦር መሳሪያ ምርታቸውን ጨምረዋል።
ሩሲም በተመሳሳይ የጦር መሳሪያ ምርቷን ማሳደጓ ተገልጿል። ሩሲያ ግን በፈረንጆቹ 2ዐ14 ተጀምሯል ላለችው ጦርነት ምዕራባውያንን ተጠያቂ አድርጋለች።
"መጎረር አልፈልግም፤ ነገርግን በጦር መሳሪያ ምርት ከምዕራባውያን እንቀድማለን" ሲሉ የመሳሪያ ምርትን የሚቆጣጠሩት የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ማንቱሮቭ ተናግረዋል።
እሽቅድምድሙ እስከመቼ ይቀጥላል ተብለው የተጠየቁት ሚኒስትሩ ከፈረንጆቹ 2025-2034 እንደሚቀጥል እቅድ ተይዟል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን እና መከላከያ ማኒስትሩ ሰርጌ ሾይጉ የከባድ መሳሪያ፣ ድሮን፣ ታንክ እና ሌሎች መሳሪያዎች ምርት መጨመሩን ተናግረዋል።
አንዳንድ የቀድሞ መሪዎች የሩሲያ 2.2 ትሪሊየን ዶላር የምዕራባውያንን ግዙፍ አቅም መቋቋም አይችልም እያሉ ናቸው።
እንደአይኤምኤፍ መረጃ ከሆነ የዚህ አመት የአሜሪካ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ገቢ 27 ትሪሊየን ዶላር ሲሆን የቻይና ደግሞ 17.7 ትሪሊየን ዶላር ነው።