ፑቲን እንደሚበቀሉ መዛታቸውን ተከትሎ ሩሲያ ዩክሬንን እየደበደበች ነው
ሩሲያ፣ በዩክሬን ዋና ከተማ ላይ ባደረሰችው መጠነሰፊ የሚሳይል ጥቃት በከተማዋ የተወሰነ ክፍል ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉ ተገልጿል
ጥቃት የተከሰተው በትናንትናው እለት ፑቲን በቤልጎሮድ የደረሰው ጥቃት ምላሽ ይሰጠዋል የሚል ዛቻ ማስማታቸውን ተከትሎ ነው
ፑቲን እንደሚበቀሉ መዛታቸውን ተከትሎ ሩሲያ ዩክሬንን እየደበደበች ነው።
የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያዋ ቤልጎሮድ ከተማ 24 ሰዎችን ገድሏል ላሉት የዩክሬን ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እንደሚሰጡ ከዛቱ ከሰአታት በኋላ ሩሲያ በኪቭ እና ካርኪቭ ከተሞች ላይ ከፍተኛ ድብደባ እያደረሰች መሆኑን የዩክሬን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ሩሲያ፣ በዩክሬን ዋና ከተማ ላይ ባደረሰችው መጠነሰፊ የሚሳይል ጥቃት በከተማዋ የተወሰነ ክፍል ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
የኪቭ ከተማ ከንቲባ ቪታሊ ክሊሸንኮ ነዋሪዎችን ከፍንዳታው ራሳቸውን እንዲያድኑ በቴሌግራም አሳስበዋል።
የዩክሬን አየር ኃይል ከእኩለ ሌሊት በኋላ ኪቭን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን ከተሞችን ኢለማ ያደረጉ 35 የሩሲያ ድሮኖችን መትቶ መጣሉን በዛሬው እለት አስታውቋል።
ይህ ጥቃት የተከሰተው በትናንትናው እለት ፑቲን በቤልጎሮድ የደረሰው ጥቃት ምላሽ ይሰጠዋል የሚል ዛቻ ማስማታቸውን ተከትሎ ነው።
ሩሲያ በበርካታ የዩክሬን ከተማች ላይ ለሰአታት የቆየ የአየር ጥቃት አድርሳለች።
ክሊሸንኮ የጋዝ ቱቦዎች መጎዳታቸውን እና በርካታ የከተማዋ ህንጻዎች የኃይል አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው ተናግረዋል።
ሩሲያ ባለፈው አርብ እለት በዩክሬን ላይ ባደረሰችው መጠነሰፊ የሚሳይል እና የድሮን ጥቃት 39 ሰዎች ተገድለዋል።
ዩክሬን ከካርኪብ ግዛት ጥቃት እንደሰነዘረችባት የምትገልጸው ሩሲያ በግዛቷ ላይ መጠነሰፊ ጥቃት አድርሳለች።
በምስራቅ ዩክሬን የምትሰነዝረውን ጥቃት ያጠናከረችው ሩሲያ፣ ባለፈው ሳምንት ማሪንካ የተባለችው ከዶኔስክ በቅርብ ርቀት የምትገኘውን ከተማ መቆጣጠሯን ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።