ሩሲያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ የተሳሳተ መረጃ የመልቀቅ ዘመቻ መክፈቷን ማይክሮሶፍት ገለጸ
ማይክሮሶፍት እንዳለው ባለፈው አመት ስቶርም-1679 የአይኦሲ አመራሮችን ለማንኳሰስ ያለመ "ኦሎምፒኩ ወድቋል"የሚል ፊልም አዘጋጅቶ ነበር
ማይክሮሶፍት እንደገለጸው ሩሲያ ፈረንሳይን እና የፓሪስ ኦሎምፒክን የሚያጠለሽ የተሳሳተ መረጃ በኢንተርኔት አማካኝነት የማሰራጨት ዘመቻ ከፍታለች
ሩሲያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ የተሳሳተ መረጃ የመልቀቅ ዘመቻ መክፈቷን ማይክሮሶፍት ገለጸ።
ማይክሮሶፍት ባለፈው እሁድ ባወጣው ጽሁፍ እንደገለጸው ሩሲያ ፈረንሳይን እና የፓሪስ ኦሎምፒክን የሚያጠለሽ የተሳሳተ መረጃ በኢንተርኔት አማካኝነት የማሰራጨት ዘመቻ ከፍታለች።
ዘመቻው የተሳሳቱ የዜና ዌብ ሳይቶችን እና የአለምአቀፉን የኦሎምፒክ ኮሚቴን(አይኦሲ) ዝና የሚሸረሽር ዶክመንተሪ ፊልሞችን የሚያካትት እና የክረምቱ ኦሎምፓክ በብጥብጥ ይስተጓጎላል የሚል ስጋት የሚጥር መሆኑን ማይክሮሶፍት ጠቅሷል።
"የሩሲያ ወዳጅ በሆኑ አካላት እየተካሄደ ካለው የማጠልሸት ዘመቻ ውስጥ ታጣቂ ኃይሎችን በማስመሰል ማስፈራሪያ የሚፈጥረው በጣም አስጨናቂው ነው" ብሏል ማይክሮሶፍት።
ሩሲያ በዚህ ጉዳይ ምላሽ አልሰጠችም ተብሏል።
ማይክሮሶፍት በ2023 መጨረሻ ላይ የሚታወቁ የሩሲያ የተሳሳተ መረጃ አሰራጮች በፓሪስ ኦሎምፒክ በሚሳተፉ እስራኤላውያን በ1972 በፍልስጤም ታጣቂዎች በሙኒክ የደረሰባቸውን አይነት ጥቃት ይፈጸማል የሚል ማስፈራሪያ በዲጂታል አዘጋጅተው ለጥፈዋል ብሏል።
ኩባንያው ዘመቻው በሩሲያ በሚደገፉት ስቶርም-1099 ወይም ዶፕሌጋንደር ተብሎ በሚታወቀው እና ስቶርም-1679 በተባሉ ሁለት አካላት እየተሰራጨ መሆኑን እንደደረሰበት ገልጿል።
ዶፕሌጋንደር እና የፈረንሳይ የዜና ድረ ገጾች የሩሲያን አይኦሲ በሙስና ተጨማልቋል እና ሁከት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚውን ስጋት አስተጋብተውታል ብሏል ማይክሮሶፍት።
ማይክሮሶፍት እንዳለው ባለፈው አመት ስቶርም-1679 የአይኦሲ አመራሮችን ለማንኳሰስ ያለመ "ኦሎምፒኩ ወድቋል"የሚል ፊልም አዘጋጅቶ ነበር።
ፊልሙ የተሰራሙ ታዋቂውን አሜሪካዊ ፊልም ሰሪ ጽምጽ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ በማስመሰል ሲሆን አላማውም ሌሎች የአሜሪካ ታዋቂ ሰዎችን በማታለል እንዲደግፉት ማድረግ ነበር።
እንደኩባንያው ከሆነ አይኦሲ የሩሰያ አትሌቶች ገለልተኛ ተወዳዳሪ ሆነው በፓሪስ ኦሎምፒክ እንዲሳተፉ ከወሰነ ከባለፈው አመት በኋላ ሩሲያ ምታደርገውን ዘመቻ አጠናክራለች።